I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
God created mankind simple. He created him and commanded him to eat everything except the tree of the knowledge of good and evil. But m...
-
We want God to use us mightily. We ask God “use me and I will do whatever it takes”. When the time to pay the price that isn’t expected...
-
በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ...
-
አቢይ ጥሞና #አንድ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡33 ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄ...
-
Believe God exists And without faith, it is impossible to please God because anyone who comes to him must believe that he exists and that ...
-
We are created by God for a specific purpose. We are created in His glory. We are not here by accident. We are created on purpose. W...
-
Singleness is a Blessing Classifying establishment according to marital status is false teaching. And one of the problems of society is t...
Monday, February 28, 2022
Sunday, February 27, 2022
Tuesday, February 22, 2022
Friday, February 18, 2022
Sunday, February 13, 2022
የፍቅር ምንጭ
ስለ ፍቅር ብዙ ይዘከራል ይወራል፡፡
ሁሉም
ሰው ይህ የሚዘመርለትንና የሚሰበክለትን ፍቅር ማወቅ ፣ መኖር እና ማጣጣም ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ወደ ተግባር ሲመጣ ፍቅር በተግባር
ሊተረጎም የማይችል ረቂቅ ነገር ብቻ ይሆንበታል፡፡
ሰው
ደግሞ እውነተኛውን ፍቅርን ካልተረዳ ተመሳሳዩን ምኞትን እንደፍቅር ይዞት ባነሰ ነገር ረክቶ ይኖራል፡፡
ፍቅር
ግን ምኞት አይደለም፡፡ ፍቅር ስሜት አይደለም፡፡ ፍቅር ከፍ ያለ የህይወት ደረጃ ነው፡፡
ስለፍቅር
የሚናገሩትን መፅሃፍት በማንበብ ፍቅር አይመጣም፡፡ ፍቅር ከሰው አይመጣም፡፡ ሰው ራሱ ፍቅርን የተራበ እና ፍቅር የሚያስፈልገው
ፍጥረት ስለሆነ ፍቅርን በራሱ ሊሰጥ አይችልም፡፡
ፍቅር
የሚመጣው ፍቅር ከሆነው ከእግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሔር
ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል። 1ኛ ዮሐንስ 4፡16
ፍቅርን
ሊያውቅ በፍቅር ሊኖር የሚችለው በእግዚአብሄር የሚኖር ሰው እግዚአብሄርም በእርሱ የሚኖርበት ሰው ብቻ ነው፡፡
ሰው
ፍቅርን ከእግዚአብሄር ካላገኘ ምኞትን እንጂ ፍቅርን በፍፁም ሊያውቀው አይችልም፡፡
ሰው
ከእግዚአብሄር ፍቅርን ካልተቀበለ ፍቅርን ተቀብሎ አያውቅም፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ፍቅር ጉልበት ካላገኘ በእውነተኛ ፍቅር ሌላውን
የሚወድበት አቅም አይኖረውም፡፡
ሰው
ምክኒያታዊ ያልሆነውን እውነተኛውን ፍቅርን መማር የሚችለው ፍቅር ከሆነው ከእግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሄርን
ፍቅር የቀመሰ ሰው ብቻ እውነተኛውን ፍቅር ያውቃል፡፡
የእግዚአብሄርን
ፍቅር የቀመሰ ሰው ብቻ የተቀበለውን ፍቅር ለሌላው መስጠት ይችላል፡፡
በተሰጠንም
በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ሮሜ 5፡5
በእግዚአብሄር
ፍቅር የረካ ሰው ብቻ ሌላውን ሰው በፍቅር ሊያረካ ይችላል፡፡
ሰው
የእግዚአብሄርን ፍቅር በተቀበለ መጠን የእንካ በእንካ ያልሆነውን ፍቅር ለሌላው መስጠት ይችላል፡፡
Abiy Wakuma Dinsa አቢይ ዋቁማ
ዲንሳ
ለተጨማሪ
ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #እምነት #ፍቅር #ስር #መሰረት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ከቅዱሳንሁሉጋር #መታበይ #መመካት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ