I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያ የ መልኩ ይከበራል ፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚ ከ ብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁ...
-
Dhalachuun Yesus Raawwii Raajichaa Ture Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deess...
-
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገ...
-
https://youtu.be/VhF0pSsp14I በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን
Sunday, February 28, 2021
Saturday, February 27, 2021
Thursday, February 25, 2021
የበለጠ የተሻለ ከፍ ያለ
ከእርስዋ
በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ። ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ። ኦሪት ዘፍጥረት 3፡5-6
እግዚአብሄር
ሰውነ ሲፈጥረው የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልቶ ነው፡፡ ሰው ግን የተሰጠውን ነገር ሳያይ ሲቀር ፣ ሲያናንቅና የተሻለ ነገር ሲፈልግ
ይሳሳታል ከእግዚአብሄርም መንገድ ይወጣል ፡፡ በየትኛውም አለም ያለው ሰው የሚፈተነው በዚህ ነው፡፡
ሰው
እንዴት ሙሉ ተደርጎ እንደተፈጠረ ሳይረዳ ሲቀር የሚፈተነውና የሚወድቀው የተሰጠውን ትቶ የተሻለ ፣ የበለጠ ፣ ከፍ ያለ ነገር ለራሱ
ሲፈልግ ነው፡፡
እግዚአብሄር
ሔዋንን ሙሉ አድጎት ፈጥሯት እያለ የሰይጣንን ንግግር ሰምታ የተሻለ እውቀትንና የበለጠ ሃይልን ፈለገች፡፡ ሔዋን ግን የሚያስፈልጋት
ባላት ሃይል መርካትና ያላትን ሃይል በሚገባ መጠቀም ብቻ ነበር፡፡
አሁን
በየእለት ህይወታችን የምንፈተነው በዚሁ ፈተና ነው፡፡
በተለይ
በክርስቶስ ኢየሱስ አምነን የእግዚአብሄር ልጆች የሆንን ሁላችን እግዚአብሄር አባታችን ሆኗል፡፡ እግዚአብሄር የሚያስፈልገን ሁሉ
በክርስቶስ ሰጥቶናል፡፡ እግዚአብሄር የሰጠንን መረዳት ሳንችን ስንቀር ሙሉ የሆነውን የእግዚአብሄርን አቅርቦት ልናሻሸለው የሚበልጥ
፣ የተሻለና ከፍ ያለ ነገር ለማግኘት ስንሞክር እንሳሳታለን፡፡
አሁን
የሚያስፈልግን ተጨማሪ ገንዘብ ሳይሆን የተሰጠንን ገንዘብ ተረድተን የምንጠቀምበት ጥበብ ነው፡፡
ለእያንዳንዱ
እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። አምስት መክሊትም የተቀበለው
ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና
የጌታውን ገንዘብ ቀበረ። ማቴዎስ 25፡15-18
አሁን
የሚያስፈልገን ተጨማሪ እምነት ሳይሆን ያለንን እምነት ማሰራት ብቻ ነው፡፡
ሐዋርያትም
ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት። ጌታም አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል
ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር። ሉቃስ 17፡5-6
አሁን
የሚያስፈልገን ተጨማሪ ዝና ሳይሆን ባለን ዝና ተጠቅመን ሰዎችን ማገልገል ነው፡፡
አሁን
የሚያስፈልገን ተጨማሪ ሃብት ሳይሆን የተሰጠንን ሃብት ለእግዚአብሄር መንግስት ጥቅም እንዴት እንደምናውለው ምሪት መፈለግ ነው፡፡
የሰይጣንም ፈተና ያለንን ርስት እንዳናይ ፣ በሌለን
ላይ እያተኮርን "በምስኪንነት" አስተሳሰብ ህይወታችንን ለምንም የማይጠቅም ሽባ ማድረግ ነው፡፡
ሰይጣን ያለንን እስከናቅን ድረስ ፣ ባለን ነገር
ላይ እርምጃ እሰካልወሰድን እና ሁልጊዜ ለተጨማሪ ፣ ለሚሻልና ለሚበልጥ ሃይል ፣ ስልጣን ፣ ሃብትና ዝና ብንሮጥ ግድ የለውም፡፡
የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡2-3
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት
#መደገፍ #ሰንበት
#አስቀድማችሁ #ፅድቁን
#ኢየሱስ #ክርስቶስ
#ጌታ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#እምነት #መፅሃፍቅዱስ
#መንፈስቅዱስ #ምህረት
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
Monday, February 22, 2021
Sunday, February 21, 2021
Life Is Like A Cup of Coffee Inspirational Video Movie
Saturday, February 20, 2021
በእምነት ያልሆነ
የሚጠራጠረው ግን ቢበላ በእምነት ስላልሆነ ተኮንኖአል፤ በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡23
ሰው
የተፈጠረው በእምነት እንዲኖር ነው፡፡ ሰው በእምነት ካልኖረ የተፈጠረበትን አላማ ይስታል፡፡ ሰው በጥርጥር ከኖረ በህይወቱ ትርጕም
ያለው ነገር ማድረግ ይሳነዋል፡፡
ሰው
የእግዚአብሄርን ስራ ሰራ የሚባለው ሲያምን ነው እንጂ ሃይማኖራዊ ወግና ስርአት ስላደረገ አይደለም፡፡
እንግዲህ፦
የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት። ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 6፡28-29
የሚጠራጠር
ሰው ከእግዚአብሄር የሚያገኘው በረከት ሙሉ አይሆንም ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄርን ስለተጠራጠረ ምንም ነገር አያገኝም፡፡
ነገር
ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። የያዕቆብ መልእክት 1፡6-8
ሰው
ካመነ በኃላ የጥርጥርን ሃሳብ እንዳያስተናገድ መጠንቀቅ አለበት፡፡ ሰው ካመነ በኃላ በእምነቱ መፅናት አለበት፡፡ ሰው ማመኑ ብቻ
ሳይሆን በእምነት መፅናቱና አለመጠራጠሩ ወሳኝ ነው፡፡ ሰው አምኖ በኃላ በእምነቱ ባይፀናና ቢጠራጠር ወደኃላም ቢያፈገፍግ በረከት
ሊያገኝ አይችልም፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤ የማቴዎስ ወንጌል 21፡21
የሰው
ሃላፊነቱ የእግዚአብሄርን ቃል በቀጣይነት በመስማት እምነቱን መገንባት ብቻ ሳይሆን እምነቱን ሊንድ የሚችለውን የጥርጥርን ኃሳብ
አለማስተናገድ ነው፡፡
ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም። ወደ ሮሜ ሰዎች 4፡20-21
ሰው እምነትን ለማግኘት ብቻ ሳይሆን እምነቱን
ለመጠበቅ የእምነት ተጋድሎን መጋደል አለበት፡፡
እምነት እግዚአብሄርን እንደሚያስደስተው ሁሉ እግዚአብሄር
በጥርጥር አይደሰትም፡፡
ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም። እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም። ወደ ዕብራውያን 10፡38
የሰው
እምነት እግዚአብሄርን እንደሚያስደስተው ሁሉ የሰው ጥርጥር ያሳዝነዋል፡፡
ያለ
እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ ዕብራውያን 11፡6
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ማየት #አለማየት
#ቃል #ጥርጥር
#የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት
#እወጃ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#መንፈስቅዱስ #ህይወት
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
Friday, February 19, 2021
Wednesday, February 17, 2021
The Deadly Sin of the Flesh
Our flesh has a sinful tendency. It doesn’t understand the
things of God. It doesn’t care about spiritual things.
The mind governed by the flesh is death, but the mind
governed by the Spirit is life and peace. The mind governed by the flesh is
hostile to God; it does not submit to God’s law, nor can it do so. Those who
are in the realm of the flesh cannot please God. Romans 8:6-8
Obviously, man is created to dominate. The man was created
to dominate in love and goodness.
So God created mankind in his own image, in the image of God
he created them; male and female he created them. God blessed them and said to
them, “Be fruitful and increase in number; fill the earth and subdue it. Rule
over the fish in the sea and the birds in the sky and over every living
creature that moves on the ground.” Genesis 1:27-28
After sin came into this world the flesh still wants to
dominate. But the flesh craves power to dominate with a distorted motive. The
wisdom of domination is corrupted.
Your heart became proud on account of your beauty, and you
corrupted your wisdom because of your splendor. Ezekiel 28:17
Now the flesh craves power not to dominate in love but in
hatred. It craves power to dominate in evil but goodness. It craves power to
dominate in selfishness, not in love.
The flesh doesn’t understand the importance of trusting the
Lord for our future. Instead, the flesh craves the power to control our future.
It doesn’t have the patience to follow the pace of God. Our sinful nature
doesn’t operate in the wisdom above but the wisdom of man.
For where jealousy and selfish ambition exist, there is
disorder and every evil thing. But the wisdom from above is first pure, then
peaceable, gentle, reasonable, full of mercy and good fruits, unwavering,
without hypocrisy. James 3:16
The flesh doesn’t want to leave the judgement of the persons
to God. It craves the power to pay back evil for evil.
Never pay back evil for evil to anyone. Respect what is
right in the sight of all men. Romans 12:17
The flesh enjoys competition with others instead of
completing God’s assignment. It likes to manipulate and control others.
If any ungodly desire is traced back, it leads to the power
crave of flesh. The flesh doesn’t appreciate the character. It just wants power
not the fruit of the spirit.
But the fruit of the Spirit is love, joy, peace,
forbearance, kindness, goodness, faithfulness, gentleness, and self-control.
Against such things there is no law. Galatians 5:22-23
The flesh sees investing time and energy in developing
character other than power crave as a waste of time. The flesh wants to have
wealth, might, or knowledge to have things its way not to give to love and to
bless. The flesh hates to trust God and to leave it in the hand of God.
The flesh doesn’t want to be accountable to God. The flesh
worships nothing but power.
Any human being's problems can be traced back to the work of
the flesh, namely, power craves. Any work of the flesh is centred in power
crave. Any manifestation of the sin of the flesh is originated in the flesh
power crave.
It inappropriately controls other people and situations
around greed, selfishness, and hatred.
We have to understand the operation of the flesh to mortify
the work of the flesh in our lives.
For if you live according to the flesh, you will die; but if
by the Spirit you put to death the misdeeds of the body, you will live. Romans
8:13
Instead, clothe yourselves with the Lord Jesus Christ, and
make no provision for the desires of the flesh. Romans 13:14
Abiy Wakuma Dinsa
For More Articles https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
#God #Jesus #knowledge #love #desire #flesh # spirit #perseverance
#trustgod #grace #salvation #church #testimony #rejoice #preaching #Bible
#theword #Abiydinsa #scriptures #abiywakumadinsa
Tuesday, February 16, 2021
ፍቅርን ፍለጋ
ሰው የተፈጠረው ፍቅር በሆነው አምላክ እግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በፍቅር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ፍቅርን እንዲቀበልና ፍቅርን እንዲሰጥ ነው፡፡
ፍቅር የሰው መሰረታዊ ፍላጎት ነው፡፡ ሰው እርሱ እንዲወደድ ይፈልፈጋል፡፡ ሰው ሌላውን መውደድ ይፈልጋል፡፡
ሰው ፍቅርን ይፈልጋል፡፡ ሰው ፍቅርን ሲያግኝ ይረካል፡፡ ሰው ፍቅርን አስካላገኘ አይረካም ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡
ሰው ፍቅርን መፈለጉ ትክክል ነው፡፡ ሰው ፍቅርን መፈለጉ በራሱ ምንም ችግር የለበትም፡፡ ሰው ፍቅርን የሚፈልግበት ቦታ ፣ ፍቅርን የሚፈልግበትን መጠን እና ፍቅርን የሚፈልግበት ሁኔታን ማወቅ አለበት፡፡
ሰው በመጀመሪያ ፍቅርን ማወቅ ያለበት ከእግዚአብሄር ጋር ነው፡፡ ሰው መጀመሪያ ፍቅርን መቀበል ያለበት ከእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ፍቅር እንዴት እንደሚቀበል እና ለእግዚአብሄር ፍቅርን እንደሚመልስ ማወቅ አለብት፡፡
ሰው የእግዚአብሄርን ፍቅር እንዴት እንደሚቀበል ካላወቀ ለእግዚአብሄር ፣ ለራሱና ለሌሎች ያለው የፍቅር ህይወቱ የተስተካከል ሊሆን አይችልም፡፡
የትኛውም እውነተኛ ፍቅር ምንጩ ፍቅር የሆነው እግዚአብሄር ነው፡፡
በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ወደ ሮሜ ሰዎች 5፡5
ፍቅርን በእግዚአብሄር ፍቅር ያልተረዳ ሰው ፍቅር ያልሆነውን ማስመሰያውን ፍቅር በማለት በፍቅር ትርጉሙ ይሳሳታል፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቅር ያላየ እና ያላወቀ ሰው የሰውን ፍቅር ቢያይም ሊያውቀው አይችልም፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቅር ያልቀመሰ ሰው የፍቅርን ትርጉም ሊረዳ በፍፁም አይችልም፡፡
እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡16
ሰው የእግዚአብሄርን ፍቅር አቀባበሉ እና ከእግዚአብሄር ጋር ያለው የፍቅር ግንኙነቱ ለእግዚአብሄርና ለሰው ያለውን ፍቅር ይወስነዋል፡፡
ሰው በእውነተኛ እርካታ የሚረካው በእግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ ሰው በእውነተኛ እርካታ የሚረካው በእግዚአብሄር በተወደደበት መወደድ እግዚአብሄርን ፣ ራሱን እና ሌላውን ሲወድድ ነው፡፡
ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው የፍቅር ግንኙነቱ ቦታውን ሲይዝ ሌሎች የፍቅር ግንኙነቶቹ ሁሉ ትክክለኛ ቦታቸውን የይዛሉ፡፡
ሌላው እንዲወደን የምንፈቅደው የእግዚአብሄርን ፍቅር መቀበል በተለማመድነው መጠን ብቻ ነው፡፡ ሌላውን መውደድ የምችለው እግዚአብሄር እንዴት እንደወደደን በመረዳት ብቻ ነው፡፡ ሌላውን የምናምነው የእግዚአብሄር በፍቅር ባመንነው መጠን ብቻ ነው፡፡
ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡7-8
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #መውደድ #ማድረግ #መስጠት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ሳምራዊ #ሌዋዊ #ካህን #ባልጀራህን #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #ወንጌል #ፅናት #ትግስት #መሪ
Monday, February 15, 2021
Deeds are Weighed
Do not keep talking so proudly or let your mouth speak such arrogance, for the Lord is a God who knows, and by him, deeds are weighed. 1 Samuel 2:3
We owe God nothing. He knows how
to compensate the unprivileged. He knows how to fill the lack. Likewise, he
knows how to encourage the discouraged.
This is what the Lord says: “Let
not the wise boast of their wisdom or the strong boast of their strength or the
rich boast of their riches, but let the one who boasts boast about this: that
they have the understanding to know me, that I am the Lord, who exercises
kindness, justice and righteousness on earth, for in these I delight,” declares
the Lord. Jeremiah 9:23-24
Our riches don't make us any
better than the poor as there is no key to the human problem in once riches.
Our education doesn't give us an unfair upper hand from the uneducated as there
is no solution for our problems in education. Someone's lack of power doesn't
make one any less than the mighty as the key of life is in God's hand not in
the rich, wise, or mighty. He is a fair judge. He judges the world in wisdom
and love.
I have seen something else under
the sun: The race is not to the swift or the battle to the strong, nor does
food come to the wise or wealth to the brilliant or favor to the learned; but
time and chance happen to them all. Ecclesiastic 9:11
God is the creator and the judge
of us all. He is a fair judge. He knows how to compensate. No one owes him
anything.
#jesus #lord #gospel #god #abiy #abiywakuma #abiywakumadinsa #judge #fair #bible #wisdom #love
Sunday, February 14, 2021
ወዳጄ ማነው ?
እነሆም፥ አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው ተነሥቶ፦ መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? አለው። እርሱም በሕግ የተጻፈው ምንድር ነው? እንዴትስ ታነባለህ? አለው። እርሱም መልሶ፦ ጌታ አምላክህን
በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው። ኢየሱስም፦ እውነት መለስህ፤ ይህን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ አለው። እርሱ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወድዶ ኢየሱስን፦ ባልንጀራዬስ ማን ነው? አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም
ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ። ድንገትም አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ አይቶትም ገለል ብሎ አለፈ። እንዲሁም ደግሞ አንድ ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ። አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥ ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፥ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት
ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም። በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና፦ ጠብቀው፥ ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ አለው። እንግዲህ ከነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነው ማንኛው ይመስልሃል? እርሱም፦ ምሕረት ያደረገለት አለ። ኢየሱስም፦ ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ አለው። የሉቃስ ወንጌል 10፡25-37
ኢየሱስ
እግዚአብሄርንና ሰውን ውደድ ስለሚለው ስለቀዳሚው ህግ እየተናገረ ነበር፡፡ አንድ የህግ መምህር እኔስ ሰውን እወዳለሁ ነገር ግን
መልሶ የሚወደኝ ሰው የለም አይነት አስተያየት አቀረበ፡፡ መልካም አደርጋለሁ ነገር ግን መልሶ መልካም የሚያደርግልኝ ሰው አላገኘሁም፡፡
ሰው መልካም እንዲደረግለት እንጂ መልካም ላደረገለት ሰው መልሶ መልካም ማድረግ አይፈልግም አይነት ቅሬታን አቀረበ፡፡
እንደ
ኢየሱስ ግን ፍቅር ማለት መልካም ለሚያደርግልህ መልካም ማድረግ አይደለም፡፡ ፍቅር ማለት መልካም ላደረገልህ መልሶ መልካም ማድረግ
ሳይሆን መልስ ሳይጠብቁ መልካም ማድረግ ብቻ ነው በማለት ይህን ታሪክ ነገረው፡፡
ወዳጅ
የሚገኝ አይደለም፡፡ ወዳጅ የምናፈራው ነው፡፡ ወዳኝነት የምንገነባው እንጂ በአጋጣሚ የሚገኝ አይደለም፡፡
ሰውን ወዳጅ የምናደርገው መልካም በማድረግ ብቻ ነው፡፡ ወዳጅ የምናፈራው ወደፊት መልካም ለሚያደርግልን ሰው መልካም በማድረግ አይደለም፡፡
ወዳጅ የምናፈራው ማልካ ላደረገልን ሰው መልካም በማድረግም አይደለም፡፡ መልካም ለማድረግ እስከተዘጋጀን ደረስ ብዙዎችን ወዳጅ ማድረግ
እንችላለን፡፡ ወዳጅ ማግኘት የተቸገረን ሰው እንደ ማግኘት ቀላል ነው፡፡ ለተቸገረ ሰው ምህረት ስናደርግና መልካም ስናደርግ ለዚያ
ሰው ወዳጁ እንሆናለን፡፡
የጠራውንም ደግሞ እንዲህ አለው፦ ምሳ ወይም እራት ባደረግህ ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ
በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ ብድራትም እንዳይመልሱልህ፥ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ባለ ጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ።
ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤
በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና። የሉቃስ ወንጌል 14፡12-14
ወዳጅነት መልካም ስናደርግለት መልሶ መልካም ለሚያደርግልን መልካም ማድረግ አይደለም፡፡
ወዳጅነት መልካም ላደረገልን መልሶ መልካም ማድረግ አይደለም፡፡
ባልንጀራ ወይም ወዳጅ ከፈለግክ አንተው ባልንጀራ ወይም ወዳጅ ሁን፡፡ ወዳጅ ከፈለግህ
ወዳጅነትህን የሚፈልግን ሰው ውደድ መልካምን አድርግ፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #መውደድ #ማድረግ #መስጠት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ሳምራዊ #ሌዋዊ #ካህን #ባልጀራህን #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #ወንጌል #ፅናት #ትግስት #መሪ
Friday, February 12, 2021
Love Beyond Valentine’s Day
be celebrated. Love shouldn’t be celebrated on a day of a year.
Love should be celebrated all 365 days of a year.
The reason that we shouldn’t be pressurized to celebrate love
on Valentine’s Day is that we have ample time to celebrate love for the rest of
the days. We can spread our love every day of the year.
In fact, it is easier to celebrate love once a year. And it
isn’t easy to celebrate love every day of the year.
It is easier to celebrate love when there is an atmosphere of
love and everyone is celebrating it. It is easier to celebrate love in the
firework. But it is possible.
Likewise, it isn’t easy to continue loving when we have to
create the atmosphere ourselves.
Actually, the people we love need our love the most in the
other 364 days of the year.
They need our love when they are at their lowest. They need
our love when they are weak. They need our love when it is difficult for them
to accept themselves. Likewise, they need our love when it is difficult for
them to accept our love. They need our love when they have low self-esteem.
They need our love when they need our forgiveness.
They need our love the more when they have a bad attitude.
Likewise, they need our love when they don’t listen to us. Likewise, they need
our love when they reject us. They need our love when we are
tempted to hate them. They need our love when they don't
feel lovable. They need our love when they complain without a valid
reason. Furthermore, they need our love when they are too proud to accept us.
They need our love when only their well-being motivates
us. They need our love when they can’t pay us back with love. Likewise, they
need our love when we don’t like when they think say and do.
Real love isn’t tested in a day. Real love is
tested every day. True love isn’t tested in a high light Real love is
tested in low light.
Abiy Wakuma Dinsa
For More Articles https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
#God #Jesus #knowledge #love #Valentine’sDay #marriage
#perseverance #trustgod #grace #salvation #church #testimony #rejoice
#preaching #Bible #theword #Abiydinsa #scriptures #abiywakumadinsa