I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያ የ መልኩ ይከበራል ፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚ ከ ብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁ...
-
Dhalachuun Yesus Raawwii Raajichaa Ture Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deess...
-
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገ...
-
https://youtu.be/VhF0pSsp14I በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን
Saturday, March 28, 2020
Sunday, March 22, 2020
Saturday, March 21, 2020
Friday, March 20, 2020
እግዚአብሔር ተቀብሎታል
በእምነት
የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ። ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል። የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 14:1-3
በዚህ ጊዜ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ መከላለያ
መንገዶች መካከል በክርስትያኖች መካከል መለያየት ይታያል፡፡ መለያየት በራሱ ክፉ አይደለም፡፡ መለያየትን ተመስርቶ እርስ በእርስ
መናናቅ እና መፈራረድ ግን ክፉ ነው፡፡
1.
ተጨማሪ ቫይታሚን የሚወስደው
የማይወስደውን አይፍድበት፡፡
2.
ሆስፒታል ሔዶ የሚመረመረው
የማይመረመረውን አይናቀው፡፡
3.
የፊት መሸፈኛ ወይም ጓንት
የሚያደርገው የፊት መሸፈኛ የማያደርገው ላይ አይፍረድበት
4.
የቤተክርስትያንን ስብሰባ የሚካፈለው
የማይካፈለውን አይናቀው፡፡
5.
የሚጨብጠው የማይጨብጠውን አይናቀው፡፡
6.
ከቤቱ የሚወጣው የማይወጣውን
አይፍረድበት፡፡
አንተም
በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡10
እንግዲህ
ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን እናስብ፤ በአንዳች ነገርም ልዩ አሳብ ቢኖራችሁ፥ እግዚአብሔር ይህን ደግሞ ይገልጥላችኋል፤ ሆኖም
በደረስንበት በዚያ እንመላለስ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡15-16
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ህይወት #የሚፈርድ #የሚያማ #ወንጌል #መውደድ #ፍቅር #የህይወትምስክርነት #መታዘዝ #ማገልገል #መውደድ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
Thursday, March 19, 2020
ዘመኑን ዋጁ
እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ
በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡15-16
በዘመናችን የሚሆን ነገር ሁሉ በእግዚአብሄር
ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚያስገርመው
ነገር የለም፡፡ ከመሆኑ በፊት ምን እንደሚሆን መቼ አንደሚሆን ለምን እንደሚሆን ሁሉ ያውቀዋል፡፡
አስገራሚ የሚሆነው ሁሉንም ለማናውቅ ለእኛ ነው፡፡
ይህ ነገር እንደመጣ ይሄዳል፡፡ ይህ ነገር ተራራ እንደሆነብን ይህ ነገር አለፈ እንዴ እንላለን፡፡
የማያልፍ የሚመስለው በቅርቡ እንደተረት ይወራል፡፡
የእኛ ሃላፊነት ከእንደዚህ አይነት ጊዜ ውስጥ የተሻለ ነገር ማውጣት ነው፡፡ የእኛ ሃላፊነት ዘመኑን ለእግዚአብሄር መንግስት መጠቀም ነው፡፡
ክፉ ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡
እግዚአብሄር ግን ክፉውን ለውጦ ለመልካምነታችን
ይጠቀምበታል፡፡
እግዚአብሔርንም
ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡28
ዘመኑን የምንገዛውና ለራሳችን ጥቅም የምንጠቀምበት
ዘጠኝ መንገዶች
1. እግዚአብሄርን ማመስገን
እግዚአብሄር
እንከን የማይወጣለት መልካም ነው፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብሄር
ምስጋና ሊመሰገን ይገባል፡፡ የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን የሚያዩ ሰዎች ሁልጊዜ እግዚአብሄርን በነገር ሁሉ ያመሰግኑታል፡፡
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር
ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡16-18
የሰው አመስጋኝነት የሚለካው በእንደዚህ አይነት ጊዜ ነው፡፡ ሰው ያለው ሃይል የሚለካው በፈተና ጊዜ ነው፡፡
በመከራ ቀን ብትላላ ጉልበትህ ጥቂት ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 24፡10
2. አለመፍራት
ፍርሃት ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡
በፍርሃት የምናደርጋቸው ማንኛውም ድርጊቶች ይጎዱናል እንጂ አይጠቅሙንም፡፡
በፍርሃት የምናደርጋቸው ነገሮች ስለእግዚአብሄር ልጅነታችን አይመሰክርም፡፡ በፍርሃት የምናደርጋቸው ነገሮች በተለምዶው ማድረግ የምንቻለችውን ነገሮች እንኳን እንዳናደርግ
ሽባ ያደርገናል፡፡
ኢየሱስ ግን ሰምቶ፦ አትፍራ፤ እመን ብቻ ትድንማለች ብሎ መለሰለት። የሉቃስ ወንጌል 8፡50
3. አለመጨነቅ
ከጭንቀት የሚጠቀመው ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ሰው ለመጨነቅ ሲፈተን ያንን ሃይል ፀሎት ላይ ማፍሰስ አለበት፡፡ ለመጨነቅ ሲፈተን ለጭንቀት የሚያባክነውን ጊዜ በፀሎት ላይ ማዋል ፍሬያማ ያደርገዋል፡፡ ለመጨነቅ ሲፈተን የጭንቀቱን ጉልበት በፀሎት ላይ ማፍሰስ ፍሬያማ ኢንቨስትመንት
ነው፡፡
ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡6
4. ሌሎችን ማበረታታት
ሰዎች ተጨንቀዋል፡፡ እኛ ደግሞ ላለመጨነቅ
100% ምክኒያት አለን፡፡ እግዚአብሄር
እረኛችን ነው፡፡ እግዚአብሄር
ጠባቂያችን ነው፡፡ እግዚአብሄር
መመኪያችን ነው፡፡ እኛ በእግዚአብሄር ቃል ተበረታተን ሰዎችን ማበረታታት ሰዎች እግዚአብሄርን በእኛ እንዲያዩ ያደርጋቸዋል፡፡
ሰዎችን ማበረታታት የእኛ መንፈስ የተለየ መንፈስ እንዳለን ያሳያቸዋል፡፡ ሰዎችን ማበተታታት ብርታት ከመስጠቱ በተጨማሪ የሌላቸውን ያንን በመንፈስ ቅዱስ የሆነ የሃይል መንፈስ እንዲፈልጉት
እንዲጓጉ ያደርጋል፡፡
በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ
ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤ በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ
በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፥ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡14-16
5. ለሌሎች መልካምን ማድረግ
ይህ ጊዜ ደግሞ ያልፋል፡፡ ሰዎች መልካም ስራችንን የሚያዩበት ወሳኝ ጊዜ ነው፡፡ ከመንገዳችን ወጥተን ለሰዎች መልካም ማድረግ እውነተኛ ሰዎች መሆናችንን ለማሳየት እና የቀመስነውን የእግዚአብሄር
መንግስት መልካምነት እንዲቀምሱ ያበረታታቸዋል፡፡
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ
ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። የማቴዎስ ወንጌል 5፡16
6. ለራሳችን ጊዜ መውሰድ
አንዳንድ ጊዜ ሳናስበው በጣም ባተሌ ከመሆናቸን የተነሳ እግዚአብሄር ራሱ ከእኛ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ይናፍቀናል፡፡ ታዲያ ህይወት ዝም በሚልበት ጊዜ ለመፀለይ የእግዚአብሄርን
ፊት ለመፈለግ መጠቀም ዘመኑን ለመግዛት ያስችለናል፡፡ ይህንን አይነት ጊዜ በቀላሉ አናገኘውም፡፡
እግዚአብሄር በዚህ አጋጣሚ ተጠቅሞ ሊያድሰን ሊለውጠን ይፈልጋል፡፡
በዚህ ጊዜ ተጠቅመን የእግዚአብሄር ቃል በሙላት እንዲኖርብን
ቃሉን ማንበብና ማሰላለስ የማይገኝ እድል ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እንደሚመስበው
ሁኔታው ሳይሆን የሚለወጠው እኛ ነን፡፡ እምነታችን ይፈተናል ይጠራል፡፡ አመለካከታችን
ይፈተናል ይለወጣል፡፡ ዋጋ አሰጣችን ይፈተናል ይለወጣል፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ
ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት። የሉቃስ ወንጌል 10፡41-42
7. ዱለት ነው ከሚሉ ጋር ዱለት አለማለት
ሰዎች በፍርሃት ጠፋን ተቆረጥን ተፈለጥን ሲሉ እኛ መፍራት ያለብን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ እኛ የምንፈራው በቂ እና ብቸኛ ፍርሃት አለን፡፡ እኛ ኮሮናን አናመልክም እግዚአብንሄርን
ብቻ እናመልካለን፡፡ እኛ ኮሮናን አንፈራም እግዚአብሄርን በፍፁም ልባችን እንፈራለን፡፡
እኛ ኮሮናን አንቀድስም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄርን እንቀድሳለን፡፡
በልባችን ልዩ ስፍራ ያለው ኮሮና ሳይሆን ክርስቶስ ነው፡፡ ኮሮናንና ክርስቶስን እኩል አንፈራም፡፡ የክርስቶስን
የዙፋን ቦታ ለኮሮና አንሰጠም፡፡
ማስፈራራታቸውንም
አትፍሩ አትናወጡም፥ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡14
8. ለሰዎች መፀለይ፡
ተስፋ ያለን ሰዎች ነን፡፡ ከምድር ያለፈ ተስፋ አለን፡፡ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች አናዝንም አንጨነቅም፡፡
በዚህ አጋጣሚ በህይወታችን
ስላለ ተስፋ ለሌሎች በየዋህነትና በፍርሃት እንመሰክራለን፡፡
በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ
ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ
ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡15
ሰዎች እንደዚህ ጊዜ ለፀሎት ክፍት የሚሆኑበት ጊዜ ላይኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ የተጨነቁ ሰዎች ስናገኝ ለእነርሱ መፀለይ ልባቸውን ወደክርስቶስ
መምራት እንዲሁም ጌታን ክርስቶስን የህይወታችንው
ጌታ እንዲያደደርጉት መምራት ይጠይቃል፡፡
9. ለፈውስ መፀለይ
አንደኛው የሚያምኑትን ከሚከተላቸው
ምልክቶች አንዱ በበሽታ ላይ ያላቸው ሃይል ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ የታመመ ሰው ስናገኝ ለዚያ ሰው መፀለይ ይጠብቅብናል፡፡
እንደዚህ አይነት አጋጣሚ በሃይል በእኛ የሚሰራውን የእግዚአብሄርን
ክብር የምንለማመድበት መልካሚ አጋጣሚ ነው፡፡
ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ። የማርቆስ ወንጌል 16፡17-18
እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም
ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር። የማርቆስ ወንጌል 16፡20
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
AbiY Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ዘመን #እድል #ዋጁ #ጥበብ #መተርጎም #ይሳኮር #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
Subscribe to:
Posts (Atom)