እግዚአብሔር
እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በሌለበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል። ትንቢተ ኤርምያስ 17፡5-6
I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያ የ መልኩ ይከበራል ፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚ ከ ብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁ...
-
Dhalachuun Yesus Raawwii Raajichaa Ture Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deess...
-
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገ...
-
https://youtu.be/VhF0pSsp14I በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን
Sunday, January 6, 2019
Friday, January 4, 2019
የወርቅ ቀለበት በእርያ አፍንጫ እንደ ሆነ፥ ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴትም እንዲሁ ናት። መጽሐፈ ምሳሌ 11፡22 ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች። መጽሐፈ ምሳሌ 31፡30
የወርቅ
ቀለበት በእርያ አፍንጫ እንደ ሆነ፥ ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴትም እንዲሁ ናት። መጽሐፈ ምሳሌ 11፡22
ውበት
ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች። መጽሐፈ ምሳሌ 31፡30
Wednesday, January 2, 2019
ንስሃ ያለመግባት አራቱ አደጋዎች
ንስሃ ማለት በአስተሳሰቡ በንግግሩና በአካሄዱ ከእግዚአብሄር ቃል የወጣ ሰው የሚያደርገው የሃሳብ ወይም የመንገድ ለውጥ ማለት ነው፡፡ እንደ እግዚአብሄር ቃል ያልኖረ ሰው ከቃሉ ሲወጣ መንገዱን ማስተካከል አለበት፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር መንገድ ተቃራኒ እየሄደ ካለ ቀኝ ኋላ ዙር ብሎ መመለስ አለበት፡፡
ሰው ግን ንስሃ ካልገባ እነዚህ አምስት አደጋዎች ከፊቱ እንደሚጋረጡ የእግዚአብሄር ቃል ያስትምራል፡፡
1. ሰው በአመፁ ንስሃ ካልገባ በስተቀር በአመፁ መቀጠሉ የማይቀር ነው፡፡
ንስሃ መግባት ሃጢያትን ከህይወት ነቅሎ እንደመጣል ነው፡፡ ሰው ከሃጢያት መንገዱ ካልተመለሰ በስተቀር ስንፍናውን ለመሸፈን ስንፍናውን መድገሙ የማይቀር ነው፡፡ ሰው ከሃጢያቱ ቶሎ ካልተመለሰ አመፃው የሰራለት ስለሚመስለው በሌላው ሰው ላይ ይደግመዋል፡፡ ሰው ሃጢያት ባሰራው በስጋው ላይ ካልጨከነ በስተቀር ሃጢያቱ ለስጋው ስለሚጥመው ደግሞ በሌላ ሰው ላይ ያሰራዋል፡፡
ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡27
ሰው በሃጢያተኛ ባህሪው በስጋው ላይ ካልጠነከረበት በስተቀር ስጋ የሃጢያት ፍላጎቱ ይበልጥ ስለሚከፈት ይበልጥ ሃጢያትን መስራት ይፈልጋል፡፡ ሰው በሃጢያቱ ንስሃ ካለገባ ሃጢያቱ በሃጢያቱ ላይ እየተከመረ ይሄዳል፡፡
ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡6-7
2. ሰው በሃጢያቱ ንስሃ ካልገባ ራሱን ያታልላል፡፡
እግዚአብሄር በሃጢያቱ ቢቀጣውም ባይቀጣውም ሰው በሃጢያቱ ንስሃ እንዲገባ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡ ሰው ግን በሃጢያቱ ንስሃ ካልገባና በአመፃ ከተሳካለት እየተታለለ ይሄዳል፡፡ ሰው ንስሃ ካልገባ ክፋት የማይሰሩ ሰዎች ሞኞች እንደሆኑ እያሰበ ይመጣል፡፡ ሰው በአመጹ ንስሃ ካልገባ ክፋት የማይሰሩ ሰዎች እንዳልገባቸው እና እንደተሸወዱ እርሱ ግን ጥበበኛ እንደሆነ ስለሚመስለው በእግዚአብሄር ጥበብ የሚኖሩትን ሰዎች ሞኝ ያደርጋል ይንቃል፡፡
ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥ ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡22
ሰው ንስሃ ካልገባ ለራሱ ጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል ነገር ግን በምድር በስጋና በአጋንንት ጥበብ ስለሚኖር ሞኝ እየሆነ ነው፡፡
ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። የያዕቆብ መልእክት 3፡15-16
3. ሰው በሃጢያቱ ንስሃ ካልገባ በዙሪያው ላሉት ሰዎች አመፅና ክፋት ትክክልኛ እንደሆነ በድርጊቱ ምሳሌ ይሆናቸዋል፡፡
ወደድንም ጠላንም የሚያዩንና ድርጊታችንን አውቀውም ይሁን ሳውቁት የሚከተሉ ሰዎች አሉ፡፡ ንስሃ የማይገባ ሰው ለሚያዩትና ለሚሰሙት መጥፎ ምሳሌ ይሰጣቸዋል፡፡ ንስሃ የማይገባና በአመፁ የሚቀጥል ሰው በአካባቢው ሰዎች በድርጊቱ አመፅ ትክክል ነው ብሎ ያስተምራቸዋል፡፡ ንስሃ የማይገባና በክፋቱ የሚቀጥል ሰው ለወንድም ለእህቶቹ ፣ ለሚስቱ ፣ ለልጆቹና ለሚመጣው ትውልድ መልካሙን እንዳይከተሉ መጥፎ ምሳሌ ይተውላቸዋል፡፡
አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡33
4. ሰው በሃጢያቱ ንስሃ ካልገባ ከመንፈስ ወቀሳና ከእግዚአብሄር ህልውና እየራቀ ይሄዳል፡፡
እንደሳተ ሲያውቅ በፍጥነት ንስሃ የማይገባ ሰው ህሊናው እየደነዘዘ አመፅ ማድረግ ይበልጥ እየቀለለው ይሄዳል፡፡
መንፈስ ግን በግልጥ፦ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡1-2
ሰው ንስሃ ካልገባ የመዳንን ደስታ እያጣው ይሄዳል፡፡ ሰው ንስሃ ካልገባ በእግዚአብሄር ህልውና ውስጥ የሚገኘውን ደስታ እያጣው ይሄዳል፡፡
አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ። የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። መዝሙረ ዳዊት 51፡10-12
ሰው በአመፃው ሲቀጥል በእግዚአብሄር ፊት ያለውን ድፍረት እያጣው ይሄዳል፡፡ ሰው በአመፃ ሲቀጥል በእምነት ኑሮያለውን ገድልና ደስታ እያጣው በሰው ሰራሽ ነገር እየተካው ይሄዳል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ጌታ #ኢየሱስ #ሃሳብ #ቃል #እግዚአብሄር #መንፈስቅዱስ #ንስሃ #መለወጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #አእምሮ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
Subscribe to:
Posts (Atom)