I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን፥ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል። 1ኛዮሐንስ 3:19-20
-
ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2 ፣6 7 ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው ስለእኛ ነው። ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው እኛ በሃጢያታችን...
-
Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deessi, maqaa isaas Amaanu'el jettee in mo...
-
Name it claim it Take it! “So Jesus answered and said to them, “Have faith in God. For assuredly, I say to you, whoever says to this mount...
-
የብልጽግና ወንጌል ምሥጢር ሲገለጥ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡16 ወንጌል በሃጢያታቸው ምክኒያት ለዘላለም ከእ...
-
ጸሎት ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ነው። ጸሎት ሊደረግ የሚችለው ከእግዚአብሄር ጋር በመግባባት ብቻ ነው። ጸሎት የሚሰምረው እንደ እግዚአብሄር አሳብ ስንጸልይ ብቻ ነው። በአጠቃላይ ለእግዚአብሄር ያለን አመለካከት ...
-
የምንሞትለት እንጂ የምንገድልለት አምላክም ሆነ ሀይማኖት የለንም! አምላክ ሀያል ነው የእኛ እርዳታ አይፈልግም። እንዲገድሉለት የሰውን እርዳታ የሚፈልግ ሀይማኖት እውነተኛ ሀይማኖት አይደለም። የሰውን እርዳታ የሚፈልግ...
-
ብዙ ጊዜ የምናተኩረው በክርስቶስ ስለተደረገልን ነገር ነው፡፡ በክርስቶስ የተደረገልን ነገር ሁሉ ያልለፋንበት ስጦታ ነው፡፡ በክርስቶስ ይህ ሁሉ ነገር ተፈደርጎልንም ለሃላፊነት የማንበቃ ህፃናት ልንሆን እንችላለን፡፡ ...
-
ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝሙር 50፡23 ምስጋና እግዚአብሄር ስለደረገልን መልካምነት ምላሽ ከመስጠት ያልፋል፡፡ ምስጋና ከእግዚአብሄር...
Monday, June 29, 2020
እግዚአብሔር ትልቅ ዘማሪት ህሊና ካሳሁን
እግዚአብሔር
፡ ትልቅ (Egziabhier
Teleq) - ህሊና ፡ ካሳሁን
፡ ትልቅ (Egziabhier
Teleq) - ህሊና ፡ ካሳሁን
ችግር
፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከሙላትህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከሙላትህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
ጭንቀት
፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከሰላምህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከሰላምህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
ድካም
፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከጉልበትህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከጉልበትህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
ማጣት
፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከዙፋንህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከዙፋንህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
ይሟሟሉ
፡ ይቀልጣሉ ፡ መገኘትህን ፡ ሲረዱ
፡ ይቀልጣሉ ፡ መገኘትህን ፡ ሲረዱ
የከበዱት
፡ ዙፋን ፡ ስጡኝ ፡ ያሉ
፡ ዙፋን ፡ ስጡኝ ፡ ያሉ
ለቀው
፡ ሄዱ ፡ እያፈሩ (፪x)
፡ ሄዱ ፡ እያፈሩ (፪x)
እግዚአብሔር
፡ ትልቅ (፬x)
፡ ትልቅ (፬x)
ከተራራው
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከከበደው
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከነገሩኝ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከችግሩ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
መንፈስ
፡ ቅዱስ ፡ ትልቅ (፬x)
፡ ቅዱስ ፡ ትልቅ (፬x)
ከጨነቀኝ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከነገሩኝ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከሰበክነው
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
ካመለኩት
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
የሰልፉ
፡ አለቃ ፡ ብቻህን ፡ ምትገዛ
፡ አለቃ ፡ ብቻህን ፡ ምትገዛ
ምድርን
፡ ፍጥረትን ፡ በቃልህ ፡ ያጸናህ (፪x)
፡ ፍጥረትን ፡ በቃልህ ፡ ያጸናህ (፪x)
ዕድሜ
፡ ማይወጣልህ ፡ ኃይልህ ፡ አይለካ
፡ ማይወጣልህ ፡ ኃይልህ ፡ አይለካ
ምሽግ
፡ መጠለያ ፡ ክንድህ ፡ የበረታ (፪x)
፡ መጠለያ ፡ ክንድህ ፡ የበረታ (፪x)
ገብተህ
፡ በእኔ ፡ ጓዳ (፪x)
፡ በእኔ ፡ ጓዳ (፪x)
ኧረ
፡ ለምን ፡ ልፍራ
፡ ለምን ፡ ልፍራ
መንፈስ
፡ ቅዱስ ፡ ትልቅ ፡ (፬)
፡ ቅዱስ ፡ ትልቅ ፡ (፬)
ከጨነቀኝ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከነገሩኝ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከሰበክነው
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
ካመለኩት
፡ በላይ ፡ ትልቅ
፡ በላይ ፡ ትልቅ
Sunday, June 28, 2020
ብዙ ጊዜ እንደምናስበው እጅግ በጣም አስፈላጊ አይደለንም በአእምሮዋችን ከምናስበው በላይ ግን ተወደናል
የእግዚአብሄር
ልጆች ነን፡፡ አስፈላጊነታችን አጠያያቂ አይደለም፡፡
ነገር
ግን ብዙ ጊዜ አስፈላጊነታችንን ከመጠን በላይ እናጋንነዋለን፡፡ ብዙ ነገሮች ካለእኛ መሰራት እንደማይችሉ በከንቱ እናስባለን፡፡
በህይወታችን
ሁሉንም ነገር ማድረግ አንችልም፡፡ ማድረግ የምንችለው በጣም ውስን ነገር ነው፡፡ ማድረግ የምንችለውን ውስኑን ነገር በትክክል ከሰራነው
ስኬታማ ነን፡፡
እኔ
ካለ እግዚአብሄር ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ እግዚአብሄር ግን ካለእኔ ሁሉን ሊያደርግ ይችላል ብሎ ትሁት መሆን ይጠቅማል፡፡ በእኛ
መጠቀም ሲፈልግ ይጠቀማል እንጂ እኛን ላይጠቀም ሌላውን ሊጠቀም ይችላል፡፡
አንገስ
ቡከን የሚባል የእግዚአብሄር ሰው ሲናገር ራሳችንን በጣም ከማጋነናችን የተነሳ ስንሞት መልከአ ምድር ሁሉ የሚለወጥ ይመስለናል፡፡
እኛ ስለሞትን የሚለወጥ መንም መልከአ ምድር አይኖርም፡፡ ለብዙ ሺዎች አመታት ምድር ቀጥላለች እኛም ስንሞት ምድር እንዳለች ትቀጥላለች፡፡
ውስን
እንደሆነን በመረዳት ራሳችንን ትሁት ማድረግ እና እጅግ አስፈላጊ በሆነው በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ በምድር ላይ ባለን ቆይታ ውጤታማ
እንድንሆን ያስችለናል፡፡
ግንድ
ሳንሆን ቅርንጫፍ እንደሆንን ስንረዳ ከእግዚአብሀጌር ጋር በሰላም እንኖራለን፡፡
እኔ
የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ
ያፈራል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡5
አካል
ሳንሆን የአካል ብልቶች እንደሆንን ስንረዳ ውጤታማነታእችን ይበዛል፡፡
አካልም
አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ
እንዲሁ ነው፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡12
እግዚአብሔር
እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና
ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥
ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 9፡23-24
ውስን
እንደሆንን በትክክል ስንረዳ ማሰብ ከሚገባን አልፈን በትእቢት እንዳናስብ ይጠብቀናል፡፡
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ
እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ። ወደ ሮሜ ሰዎች
12፡3
ውስን እንደሆንን ስንረዳ ሌላውን በትህትና ከእኛ እንደሚሻል አድርገን መቁጠር እና ማድነቅ እንጀምራለን፡፡
ውስን
እንደሆንን ስንረዳ በሁለንተናችን እኛ እግዚአብሄር ለእኛ እንደሚያስፈልገን በትህትና ማየት እንጀምራለን፡፡
እንደምናስበው
ከሚገባው በላይ በጣም አስፈላጊ አለመሆናችን ብቻ ሳይሆን ከምናስበው በላይ ተወደናል፡፡
እግዚአብሄር
ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን ፍቅር ተረድተን አንጨርሰውም፡፡
ፍቅር
የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡8
በእኛ
ላይ ያለው አላማ ፍቅር ነው፡፡
በእኔ
ላይ ያለው ዓላማውም ፍቅር ነው። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 2፡4
ጠላቶች
ሳለን ወደደን፡፡
ነገር
ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ወደ ሮሜ ሰዎች 5፡8
ሃጢያተኞች
ሳለን አንድ ልጁን እስኪሰጠን ድረስ ወዶናል፡፡
በእርሱ
የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
የዮሐንስ ወንጌል 3፡16
እራሱ
ፍቅር በሆነው በእግዚአብሄር ተወደናል፡፡
ከቅዱሳን
ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ
ትበረቱ ዘንድ፥ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፡18-19
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #እምነት #ፍቅር #ትህትና #መዋረድ
#አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ከቅዱሳንሁሉጋር #መታበይ #መመካት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
Subscribe to:
Posts (Atom)





