I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
የሚበድል ሰው ያልገባው ነገር አለ፡፡ የሚበድል ሰው የተሳሳተው ነገር አለ፡፡ የሚበድል ሰው የጎደለው እውቀት አለ፡፡ የሚበድል ሰው የጠፋበት መንገድ አለ፡፡ የሚበድል ሰው የሚያደርገውን ...
-
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡16 ሃጢያት ያታልላል፡፡ ...
-
1. ለጭንቀት የእግዚአብሄር ፅድቅና መንግስቱን ለመፈለግ በቀን 24 ሰአት 7 በሳምንት ሰባት ቀን አለን፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን ከመፈለግ የሚተርፍ እና ለጭንቀት የሚሆን አንድ ...
-
ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል ! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው። ምሳሌ 16፡16 ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፤ በወርቅና ...
-
መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ዘካርያስ 4:6 v አንድን ነገር እ...
-
… From Oppressive Obligations to Incredible Opportunities The phone isn’t just ringing, it seems to be screaming. You’ve got yet another...
Tuesday, October 11, 2022
Sunday, October 2, 2022
ርህራሔ የሌለበት የኢሬቻ አስተያየት
Saturday, October 1, 2022
የአዲሱ ኪዳን ፀሎት ትኩረት
ክርስቶስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ ከሞተ እና በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ የምንኖርበት ኪዳን በኢየሱስ የተደረገው አዲስ ኪዳን ነው፡፡
ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በሃጢያታችን ምክኒያት
ከእግዚአብሄር ጋር ጠላቶች ነበርን፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለሃጢያታችን በመሞት ከእግዚአብሄር ጋር አስታርቆናል፡፡ አሁን ከእግዚአብሔር
ጋር ሰላም ነን፡፡
ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞት በብሉይ ኪዳን ለጥቂት
ለተመረጡ ሰዎች ይሰጥ የነበረውንም መንፈስ ቅዱስን እርሱን ለተቀበልን ለሁላችንም እንዲሰጠን እና መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን አንዲኖር
አስችሎናል፡፡
ከእግዚአብሄር ጋር ጥል በነበሩበትና በክርስቶስ
ደም ባልታረቁበት ጊዜ የሚፀለየውን ፀሎቶች በዚህ በአዲሱ ኪዳን ብንፀልይ ውጤታማ አንሆንም፡፡
በአዲሱ ኪዳን የተፀለየውን አንዱን ፀሎት ለምሳሌ
ብንወስድ ፀሎቱ የሚያተኩረው ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሰራልንን ስራ በመረዳት ላይ ነው፡፡
የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡17-19
ይህ አይነቱን ፀሎት ፍሬያማ የሚያደርገው በመስቀል
ላይ የተሰራውን ስራ እውቅና መስጠቱ ነው፡፡ እንዲሁም ይህን ተሰርቶ የተጠናቀቀውን ስራ በሚገባ እንድንረዳ አይናችን እንዲከፈት
እግዚአብሄርን መለመኑ ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱ የአዲስ ኪዳን ፀሎት እግዚአብሄርን በማወቅ የጥበብ እና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጠን
ይጠይቃል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa