የህይወት ስኬት የሚመጣው ለእግዚአብሄር ቃል የመጀመሪያውን ስፍራ በመስጠትና በቃሉ ከባቢ ውስጥ ለመኖር በመወሰን ነው፡፡
ምስጉን
ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙረ ዳዊት 1:1-3
የዚህ
ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ
1፡8
የእግዚአብሄር ቃል ብቸኛ ተስፋችን ነው፡፡ ህይወታችን
ከተለወጠ የሚለወጠው በእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም። ዕብራውያን 4፡12-13
ስለዚህ ነው ለእግዚአብሄ ቃል በህይወታችን የመጀመሪያውን
ስፍራ የምንሰጠው፡፡ ከእግዚአብሄር ቃል ጋር የሙጥኝ የምንለው ስለዚህ ነው፡፡
ስለዚህ ነው በምናደርገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሄር
ቃል ከባቢ ውስጥ መኖርን የምንፈልገው፡፡ ከእግዚአብሄር ቃል ከባቢ ውስጥ በፍፁም መውጣት የማንፈልገው የተፈጠርንበትን አላማ መፈፀም
የምንችለው በቃሉ አማካኝነት ብቻ ስለሆነ ነው፡፡
እግዚአብሄርን በህይወታችን ብቸኛ አማራጭ ለማድረግ
በህይወታችን የእግዚአብሄርን ቃል ብቸኛ አማራጭ ማድረግ ይጠይቃል፡፡
እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤ አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። ዘዳግም 6፡4-9
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ማየት #አለማየት
#ቃል #ጥርጥር
#የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#መንፈስቅዱስ #ህይወት
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment