I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
የሚበድል ሰው ያልገባው ነገር አለ፡፡ የሚበድል ሰው የተሳሳተው ነገር አለ፡፡ የሚበድል ሰው የጎደለው እውቀት አለ፡፡ የሚበድል ሰው የጠፋበት መንገድ አለ፡፡ የሚበድል ሰው የሚያደርገውን ...
-
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡16 ሃጢያት ያታልላል፡፡ ...
-
1. ለጭንቀት የእግዚአብሄር ፅድቅና መንግስቱን ለመፈለግ በቀን 24 ሰአት 7 በሳምንት ሰባት ቀን አለን፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን ከመፈለግ የሚተርፍ እና ለጭንቀት የሚሆን አንድ ...
-
ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል ! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው። ምሳሌ 16፡16 ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፤ በወርቅና ...
-
መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ዘካርያስ 4:6 v አንድን ነገር እ...
-
… From Oppressive Obligations to Incredible Opportunities The phone isn’t just ringing, it seems to be screaming. You’ve got yet another...
Tuesday, June 29, 2021
Tuesday, June 22, 2021
ለፀፀት እንቢ እንበል!
ፀፀት አንድ ሰው በሠራው ነገር ወይም አንድን ነገር ባለማድረጉ የሚሰማው የሐዘን ወይም የቁጭት ስሜት ነው፡፡
ህይወት በውሳኔ የተሞላ ነው፡፡ በህይወታችን በየደቂቃውና
በየሰከንዱ ቅድሚያ የሚሰጠውን ነገር በመለየት ሂደት ብዙ ውሳኔዎችን እንወስናለናን፡፡ በህይወታችን ትንሽ ከሚባለው ነገር ጀምሮ
ትልቅ እስከሚባለው ውሳኔ ድረስ አማራጮችን አመዛዝነን ውሳኔዎችን እንወስናለን፡፡
በየቀኑና በየደቂቃው አንድን ነገር ለማድረግ ወይም
ላለማድረግ መወሰን ተፈጥሮአዊ ግዴታ ነው፡፡ አንድን ነገር ለማድረግ በወሰንን በዚያው ቅፅበት ሌላውን አማራጭ ላለማድረግ እየወሰንን
ነው፡፡ አንድን ነገር ላለማድረግ በወሰንን ቅፅበት ሌላውን አማራጭ ለማድረግህ እየወሰንን ነው፡፡
ውሳኔ ስንወስን ያለንን እውቀት ፣ ማስተዋል እና
ጥበብ ሁሉ ተጠቅመን እንወስናለን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የምንወስነው ላለንበት ጊዜ እና ላለንበት ሁኔታ የተሻለውንና ትክክል የሆነውን
ውሳኔ ነው፡፡ ለነበርንበት ሁኔታ ከዚያ ከወሰነው ውሳኔ በላይ ልንወስን እንችልም ነበር፡፡
ታዲያ ችግሩ የሚመጣው የህይወት ተግዳሮት ሲደርስብን
አንድ ቀን የወሰንነውን ውሳኔ መጠራጠር ስንጀምር ነው፡፡
ልጆች ሆነን አደጋ ስለ ደረሰበት ልጅ ወላጆቻችን
ሲያወሩ እንሰማ ነበር፡፡ ታዲያ ልጁ አደጋ ሳይደርስበት በፊት የጠየቀው ጥያቄ ፣ የፈለገው ፍላጎት እና የለመንው ልመና ሁሉ ለፀፀት
ምክኒያት ሆኖ ሲቀርብ እንሰማ ነበር፡፡ ልጁ ሱቅ ከመላኩ በፊት እማዬ ርቦኛል ብሎ እናቱ ምሳ አልደረሰም ስትመጣ ትበላለህ ብላው
ከሄደ ምነው በሰጠሁትና በበላ ኖሮ ብላ ትፀፀታለች፡፡
ደግም እንፀፀት ካልን የማይፀፅት ነገር የለም፡፡
ለፀፀት ፊት ከሰጠነው በቁማችን ሊውጠን የሚችል ክፉ ሃይል ያለው ነገር ነው፡፡
የሰውን ህይወት ለመስረቅ ለማረድና ለማጥጭፋት
ፀፀተን የሚጠቀመው ሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣን እኛን ለማሰቃየት ብዙ የህይወትን ተግዳሮት ያለፍንባቸውን ውሳኔዎች አይጠቀምባቸውም፡፡
በህይወታችን የወሰናቸውን አያሌ ውሳኔዎች እኛን ፀፀት ውስጥ ለመክተት ብዙ ጊዜ አይመቹትም፡፡
ነገር ግን የሰይጣን ብቸኛ አላማ መስረቅ ማረድና ማጥፋት ስለሆነ እንደ አጋጣሚ
ከውሳኔያችን በኋላ የተፈጠረውን ነገር ግን ከውሳኔያችን ጋር ምንም የማይገናኘውን ሁኔታ እያስታወሰ ሊያሰቃየን ይሞክራል፡፡ የሰይጣን
አላማ እኛን ዝቅ ዝቅ ማድረግህ ነው፡፡ የሰይጣን አላማ እኛን በፀፀት ሽባ እድርጎ ዛሬን እና ነገን ለእግዚአብሄር እንዳንኖር ማድረግ
ነው፡፡
እግዚአብሄር ይመራናል ያስጠንነቅናል እንጂ በፀፀት አያሰቃየንም፡፡
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን
ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል። 2ኛ ቆሮንቶስ 7፡10
አብዛኛውን ጊዜ የምንንፀፀትበት ነገር እግዚአብሄር የሌለበት ነገር ነው፡፡ የእግዚአብሄር
መንፈስ ወቀሳ የሚያበረታታ ፣ የተሻልን ሰዎች እንድንሆን የሚያደርግ እና የተሻለ አድርጎ የሚያስነሳ እና ተስፋ የሚሰጥ እንጂ ባለፈው
ህይወታችን ውስጥ በፀፀት በመኖር ዛሬን እና ወደፊታችንን እንድናባክነው የሚያደርግ አይደለም፡፡
ለፀፀት እንቢ እንበል!
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ፀፀት #መካድ #መታለል #ታማኝነት #ክህደት #ንስሃ #ሃዘን #መመለስ #መሰደድ #ሃዋሪያዊ #መውደቅ #አለመመረጥ #ተቀባይነትማጣት #ዋጋአሰጣጥ #አእምሮ #ልብ #ኢየሱስ #ጌታ #መፅሃፍቅዱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አምልኮ #እምነት #መከተል
Wednesday, June 9, 2021
መተቸት በጣም ቀላል ነው ፡፡ ሰዎች ሲተቹ እሰማለሁ እናም ስለ መሪዎቻችን እንደማይጸልዩ አውቃለሁ; ስለ ሌሎች በምንጸልይበት ጊዜ እነሱን ለመንቀፍ በጣም ተስማሚ አይደለንምና ፡፡ እኛ ክርስቲያኖች ግን ፖለቲካን ከክርስቶስ በፊት ማስቀደም የለብንም ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ከመጠን በላይ በፖለቲካ አስተሳሰብ ውስጥ በመያዛቸው የተነሳ ጥሩ መንፈሳዊ ሰዎች መሆን አይችሉም ፡፡ ኬኔዝ ኢ ሀጊን የሚማልዱ ክርስትያኖች It's so easy to criticize. I hear people criticize and I know they are not praying for our leaders; for when we pray for others we are not so apt to criticize them. As Christians, however, we are not to put politics before Christ. Some people are so politically minded they are no good spiritually. Kenneth E Hagin The Interceding Christians
መተቸት
በጣም ቀላል ነው ፡፡ ሰዎች ሲተቹ እሰማለሁ እናም ስለ መሪዎቻችን እንደማይጸልዩ አውቃለሁ; ስለ ሌሎች በምንጸልይበት ጊዜ እነሱን ለመንቀፍ በጣም ተስማሚ አይደለንምና ፡፡
እኛ
ክርስቲያኖች ግን ፖለቲካን ከክርስቶስ በፊት ማስቀደም የለብንም ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ከመጠን በላይ በፖለቲካ አስተሳሰብ ውስጥ በመያዛቸው የተነሳ ጥሩ መንፈሳዊ ሰዎች መሆን አይችሉም ፡፡ ኬኔዝ ኢ ሀጊን የሚማልዱ ክርስትያኖች
It's
so easy to criticize. I hear people criticize and I know they are not praying
for our leaders; for when we pray for others we are not so apt to criticize
them.