I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
በአሁኑ ጊዜ ሰዎች እግዚአብሄር የሚኖርበት ነው ብለው የሚያስቡትን ቤት ዋጋው እጅግ ውድ በሆነ በወርቅና በከበረ ድንጋይ ያሳምሩታል ያስጌጡታል፡፡ እግዚአብሄርም ቤቱ ውስጥ መጥቶ እንዲኖር ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ...
-
ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለልንን የሃጢያት እዳ ለእኛ ነው ብለን የተቀበልነው ሁላችን የእግዚአብሄር ልጆች ሆነናል፡፡ ንጉሱ እግዚአብሄር ወደቤተሰቡ ተቀብሎናል፡፡ እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ የሆነ ዋጋ አሰጣጥና የክብር ...
-
አንተስ የአሁድ ንጉሥ ከሆንህ፥ ራስህን አድን እያሉ ይዘብቱበት ነበር። ሉቃስ 23፡37 የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና። ዋ፥ ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም ...
-
በመንፈስ መመላለስ እጅግ ርቆ ያለ ጥቂቶች ብቻ ሊደርሱበትና ሊገቡበት የሚችሉ ልምምድ አይደለም፡፡ በመንፈስ መመላለሰ ማንኛውም በጌታ ኢየሱስ አዳኝነት ያመነ ሰው ሁሉ ሊለማመደው የሚችል የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምንፈፅ...
-
እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም። 2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፡ 3- 4 ...
-
እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት። ዘፍጥረት 2፡18 ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ሲል እግዚአብሔር የፈጠረው ሰው ...
-
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16-18 በሁሉ አመስግኑ የሚለው አባባል ለስጋችን ቀላል አይደለ...
-
ሰው ወይ ራሱ መቻል አለበት ወይም ደግሞ በሚችለው መታመን አለበት፡፡ ራሱ የማይችለው ወይም በሚችለውም የማይታመን ሰው ይወድቃል፡፡ እግዚአብሄር ሁሉን ይችላል፡፡ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሄር የሚታመን ሰው ሁሉ...
-
ብዙ ሰዎች ለመዳን በመልካም ስራቸው ላይ ይደገፋሉ፡፡ መዳንን ሲያስቡ መልካም ስራዬ ያድነኝ ይሆንን ብለው ስለመልካም ስራቸው ጥንካሬ ይጨነቃሉ፡ ፡ መልካም ስራ መስራት እንደማያድን እና ሰው ለመዳን መልካም ስራ እንደሚ...
Thursday, April 29, 2021
Wednesday, April 28, 2021
Wednesday, April 21, 2021
የልጅነት ስልጣን ክፍል ሁለት
\ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡12
እንዲህም አላቸው ሰይጣንን
እንደ መብረቅ
ከሰማይ ሲወድቅ
አየሁ። እነሆ፥
እባቡንና ጊንጡን
ትረግጡ ዘንድ፥
በጠላትም ኃይል
ሁሉ ላይ
ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥
የሚጐዳችሁም ምንም
የለም። የሉቃስ
ወንጌል 10፡18-19
ክርስቶስ ኢየሱስን አንደ አዳኝና ጌታችን የተቀበልን
ሁላችን ከጨለማው ግዛት ድነን ወደፍቅሩ ልጅ መንግስት ተሻግረናል፡፡
እርሱ
ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፡13-14
ሰይጣን ደግሞ እንደገና በባርነት ውስጥ ሊከተን
ይጥራል፡፡ በሰይጣን ጥቃት ውስጥ ላለመውደቅ ሰይጣንን አጥብቀን መቃወም ይኖርብናል፡፡
መስረቅ ማረድና ማጥፋት ብቸኛው የሆነው ሰይጣን
ዲያቢሎስን በልጅነት ስልጣናችን በቀጣይነት ልንቃወመው ይገባል፡፡
የልጅነት ስልጣናችንን ተጠቅመን ከእኛና እግዚአብሄር
የእኛ ከሆኑት ነገሮች ሁሉ ላይ ካልተቃወምነው እርሱ ራሱ አውቆ ይሄዳል ብለን መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡
በህይወታችን ለእግዚአብሄር በመገዛት ዲያቢሎስን
ከህይወታችን ከአገልግሎታችን ሁሉ መቃወም ግድ ይላል፡፡
እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ የያዕቆብ መልእክት 4፡7
ሰይጣን በክርስቶስ የመስቀል ላይ ስራ የተሸነፈ
ጠላት በመሆኑ በሚገባ ስንቃወምው መሸሽ አንጂ ሌላ ምንም እድል የለውም፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ስልጣን #ስልጣን #መቀመጥ
#ሰማያዊ #በክርስቶስ
#በጌታ #እምነት
#መደገፍ #ሰንበት
#በመንፈሴ #በሃይል
#በብርታት #ፀጥታ
#መመለስ #ማረፍ
#ፅድቁን #ኢየሱስ
#ክርስቶስ #ጌታ
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ
#መንፈስቅዱስ #መታመን
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
Tuesday, April 20, 2021
የልጅነት ስልጣን ክፍል አንድ
የልጅነት ስልጣን ክፍል አንድ
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡12
እንዲህም አላቸው ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። የሉቃስ ወንጌል 10፡18-19
የሰው ልጅ በእግዚአብሄር መልክና አምሳል የተፈጠረው እንዲገዛ ነበር፡፡
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26
ሰው ይገዛ የነበረው ለእግዚአብሄር በመገዛት ስለነበረ ሰው ለእግዚአብሄር መገዛት ሲያቆም እና በሃጢያት በእግዚአብሄር ላይ ሲያምፅ ከእግዚአብሄር ጋር የነበረውን የልጅነት የመግዛት ስልጣኑን አጣው፡፡
ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ስለተለያየ በሃጢያት በሚመላለስበት ጊዜ ሁሉ በሰይጣን ስልጣን ስር ወደቀ፡፡ በዚህ ምክኒያት ሰይጣን በእግዚአብሄር ላይ ባመፁ ልጆች ሁሉ ላይ ስልጣን ነበረው፡፡
በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡1-2
የጠላት ዲያቢሎስ ስራ ደግሞ መስረቅ ማረድና ማጥፋት ብቻ ነው፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
ክርስቶስ ኢየሱስ ደግሞ ወደምድር የመጣው የዲያቢሎስን ስራ ለማፍረስ ነው፡፡
ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡9
ክርስቶስ ኢየሱስ ሰይጣንን በመስቀል ላይ አሸንፎታል፡፡
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡15
ኢየሱስ ሰይጣንን በመስቀል ላይ ያሸነፈው ለራሱ አይደለም፡፡ ኢየሱስ ሰይጣንን በመስቀል ላይ ያሸነፈው እኛን ወክሎ በእኛ ፋንታ ለእኛ ነው፡፡
ክርስቶስ ኢየሱስን የተቀበልን ሁላችንን ከሰይጣን ስልጣን ድነናል፡፡
እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፡13-14
ኢየሱስ ክርስቶስን እንደአዳኙና ጌታው የተቀበለ ሰው ሁሉ የእግዚአብሄር ልጅነት ስልጣን አለው፡፡ ከእግዚአብሄር የተወለደ ሁሉ አለምን የሚያሸንፍበት ስልጣንን ተቀብሎዋል፡፡
እንዲህም አላቸው ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። የሉቃስ ወንጌል 10፡18-19
እግዚአብሄር በጠላት ምድር ላይ ክርስቶስን እንድንከተል እና በምድር ላይ እንድናገለግለው ሲያዘን ካለስልጣን አይደለም፡፡ የምንኖረው ሰይጣን አስኮናኞች ኑሩ ብሎ ስለፈቀደልን አይደለም፡፡ የምንኖረው በሰይጣን ችሮታና ምህረት አይደለም፡፡ ሰይጣን ወደደም ጠላም የምንንኖረው በስልጣን ነው፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ስልጣን #ስልጣን #መቀመጥ #ሰማያዊ #በክርስቶስ #በጌታ #እምነት #መደገፍ #ሰንበት #በመንፈሴ #በሃይል #በብርታት #ፀጥታ #መመለስ #ማረፍ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ