I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገ...
-
Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deessi, maqaa isaas Amaanu'el jettee in mo...
-
ያላችሁም ይብቃችሁ ! አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ። አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤ ወደ ዕብራውያን 13:5 ሰዎች ...
-
ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያ የ መልኩ ይከበራል ፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚ ከ ብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባ...
-
የክህነት ህይወት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ The Life of Priesthood Abiy Wakuma Dinsa
-
We hear this kind of saying from time to time. And we sometimes say it or are tempted to say it, especially after we are betrayed by a ve...
-
Dhalachuun Yesus Raawwii Raajichaa Ture Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deess...
-
እንግዲህ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ። እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። 2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፡1፣3 ኢየሱስ ጌታ ነው ብለን...
Saturday, November 13, 2021
How are you soending your life?
How are you spending your life?
Life is a once off gift. How are you spending your life on is the most important question.
Whether you can spend a lot of money or not the most important questions is how are you spending your life.
You can have an extensive knowledge to live by and the most important question is still how are you spending your life.
You can be powerful and famous in the world. You can have a lot of followers. What you say goes viral. The most important question is still what are you spending your life on?
It is not what you have but how are you spending it on. How are you using it for.
The most important question is what is your value setting.
What do you value the most in life.
Do you value God and the things of God?
Do you value to please God more than anything?
Do you value value to live according to the word of God ?
Thursday, November 11, 2021
ብዙ ጊዜ ከምናስበው በላይ ተወደናል አንዳንድ ጊዜ እንደምናስበው በጣም አስፈላጊ አይደለንም
ብዙ ጊዜ ከምናስበው በላይ ተወደናል አንዳንድ ጊዜ እንደምናስበው በጣም አስፈላጊ አይደለንም
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡3
አንዳንድ
ጊዜ አስፈላጊ ከሆነውም በላይ አስፈላጊ እንደሆንን ይሰማናል በዚያም ራሳችንን ከመጠን በላይ ከፍ ከፍ እናደርጋለን፡፡ አንዳንድ
ጊዜ የሰማይን አምድ ደግፈን እንደያዝን እኛ ብንለቀው ሰማይ እንደሚከሰከስ ይሰማናል፡፡
አንገስ
ቡከን የተባለው የደቡብ አፍሪካው ሰባኪ ሲናገር የራሳችንን አስፈላጊነት በጣም ከማጋነናችን የተነሳ ስንሞት መልከአ ምድር ሁሉ የሚለወጥ
ይመስለናል፡፡ ነገር ግን ስንሞት ነገሮች እንደበፊቱ ይቀጥላሉ ይላል፡፡
ለምድር
የምናበረክተው ትልቅ አስተዋፅኦ አለ ነገር ግን እኔ ካልሰራሁት እግዚአብሄር አለቀለት የሚል አስተሳሰብ ትክክልኛ አስተሳሰብ አይደለም፡፡
እኛ ግዴታ አይደለንም፡፡ ስንሄድ ሌላ ሰው አለው፡፡ ምንም ባይመስል ሙሴ ሲሄድ እንኳን በኢያሱ ተተክቶ ነበር፡፡
በሌላ
በኩል ደግሞ ብዙ ጊዜ ከምናስበው በላይ በእግዚአብሄር ወደናል፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቅር ተረድተን አንጨርሰውም፡፡ እግዚአብሄር ለእኛ
ያለውን ፍቅር የተረዳነው በከፊል ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር እጅግ ይወደናል፡፡
እግዚአብሄር
ምን ያህል እንደሚወደን ብንረዳ ጭንቀት ከህይወታችን ፈፅሞ ይሞት ነበር፡፡
ብዙ
ጊዜ ከምናስበው በላይ ተወደናል በፍቅሩ እንኑር፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንደምናስበው በጣም አስፈላጊ አይደለንም ራሳችንን ትሁት እናደርግ
በእረፍት እንኑር፡፡
ብዙ
ጊዜ ከምናስበው በላይ ተወደናል አንዳንድ ጊዜ እንደምናስበው በጣም አስፈላጊ አይደለንም፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት
#ፍቅር #የክርስቶስፍቅር
#ስር #መሰረት
#ትእዛዝ #መስጠት
#ሃሳብ #አማርኛ
#ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ልብ
#ቸርነት #ትግስት
#ፍርሃት #ደስታ
#ሐዋርያ #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#መውደድ #ትግስት
#መሪ
Monday, November 8, 2021
Sunday, October 31, 2021
Thursday, October 28, 2021
Tuesday, October 26, 2021
Sunday, October 24, 2021
Monday, October 18, 2021
የሰላም ጥሪ
በታሪክ ሂደቶች ውስጥ ሰው ከሰው ጋር ፣ ቤተሰብ ከቤተሰብ
ጋር ፣ ሀገር ከሃገር ጋር ወዘተ ይጋጫል። ለምን ተጋጩ አይባልም። ተጋጩ ማለት ደግሞ በቃ አለቀላቸው እስኪጨራረሱ ድረስ ችግራቸው መፍትሄ አያገኝም ማለት አይደለም። ተጋጩ ማለት ደግሞ አንዱ ሌላው ላይ አይሎበት እስኪያሸንፈው ድረስ ምንም መፍትሄ የለም ማለት አይደለም።
ከግጭት በኋላ ህይወት አለ ከግጭት በኋላ አብሮ መኖር አለ። ግጭት በሚገባ ከተያዘ ከግጭት በኋላ አንድነት ሊመጣ ይችላል።
የተጋጨ ቤተሰብ ሰላም ይፈጥራል በተለይ አብሮ የሚኖር ቤተሰብ ብዙ ነገር ስለሚያገናኘው ጠላትነት ይቅርብኝ አይጠቅመኝም ብሎ በመረዳት ጠላትነትን ይተዋል። ለሌላው ጥቅም ሲባል ያን ያህል የማይጎዳውንም ነገር ይተዋል። አንድነትን እና አብሮ መኖርን የሚያስብ ሰው ይነጋገራል ፣ ይታረቃል እንዲሁም
በሚያስማሙት ጉዳዮች ላይ እንደገና አብሮ መስራት ይወስናል።
የተለያየ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር በአንድነት ለመኖርም ፈልጎም ደግሞም የእኔ መንገድ ብቻ ይሁን ብሎም ሰላም ሊገኝ አይችልም። አብሮ መኖር ሌላውን በቅንነት መቀበል ፣ መደራደር ሰጥቶ
መቀበልንም ይጠይቃል።
መታረቅ ማለት አንዱ የአንዱን ውድቀት አለመፈለግና አንዱ ለአንዱ ጥፋት አለመስራት ማለት እንጂ ሌላው ወገን የሚለውን ሁሉ እሺ ብሎ መቀበል ማለት አይደለም። ብዙ ሰዎች እርቅ የሚያስደነግጣቸው ሌላው ወገን የሚጠይቀውን ሁሉ የሚቀበሉ ስለሚመስላቸው ነው። መቀራረብ መነጋገር ማለት አንዱ የሌላውን ስጋት መስማት ፣ ፍላጎቱን ለመረዳት መሞከር አብሮ ለመኖር በተቻለ አቅም የሌላውን ስጋት ለመቀነስ መወሰን ማለት ነው።
አሁንም በኢትዮጲያ ውስጥ ከሞላ ጎደል አንድ አመት የሞላው ጦርነት እየተካሄደ ይገኛል። ይህ ጦርነት ክቡሩን የሰው ህይወት እየቀጠፈ ፣ ጥላቻ ቂምና
በቀልን እያስፋፋ ፣ ብዙዎችን ለአመታት ከኖሩበት ቤታቸው እያፈናቀለ በሁለቱም ወገኖች ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድመት እያደረሰ ይገኛል።
በኢትዮጲያ መንግስትም ሆነ በህወአት በኩል እስካሁን ጎልቶ የሚታየው ሁለቱም ያላቸውን የተሻለ ጥቅም ተጠቅመው ጦርነቱን ለማሸነፍ መጣጣር ብቻ ነው። አሁን የሚታየው አንዱ አንዱን በማሳነስ ለማጥፋት እና ለመግደል መዘጋጀት ነው። አሁን የሚታየው አንዱ ለአንዱ የሚያኮስስ ስም በመስጠት አንዱ ሌላውን ከሰውነት ደረጃ ማሳነስ ነው። አሁን የሚታየው አንዱ ሌላውን ነገር እንደማይገባው ፣ ደንቆሮ እንደሆነ
በእብደት እየተንቀሳሰቀ እንዳለ ማሳየት ነው። አሁን የሚታየው አንዱ ሌላውን የስልጣን ጥመኛ እንደሆነ እና ስልጣኑን ለማስጠበቅ ሲባል ምንም ነገር እንደሚያደርግና የሰው ጥፋት ግድ እንደማይለው መካሰስ ነው። አሁን የሚታየው እንዱ ሌላውን ስግብግብና ራስ ወዳድ እንደሆነ የሌላን ጥቅም ከግምት ውስጥ ሊያስገባ እንዳልተዘጋጀ መወነጃጀል ነው።
ለህዝብ ደህንነት ግድ የማይላቸው ጥቂት የፖለቲካ መሪዎች ሌላውን ከምድረገፅ ለማጥፋት ተከታዮቻቸውን ማነሳሳትና ማዝመት ከተራ የፖለቲካ ጥቅም የዘለለ እናገለግለዋለን ለሚሉትን ህዝብ የሚጠቅመው ነገር አንዳች ፋይዳ የለውም።
ይህ ስልት በጦርነቱ ህይወቱን እና አካሉን የሚያጣውን ዝቅተኛውን የህብረተሰብ ክፍል በጥላቻ ለማነሳሳት እና ለማዝመት ይጠቅም ይሆናል። ይህ አካሄድ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ፣ በዚህ ውድድር
በበዛበት አለም አገሪቱ ከድህነት እንድትወጣ ፣ በኢኮኖሚ ራስዋን
እንድትችል ለማድረግ የሚጠቅመው ምንም ፋይዳ የለም።
እውነት ነው መቼም ቢሆን ሊወጋን ሊገድለን የመጣን ወገን እጃችንን አጣጠፈን አስኪገድለን ድረስ አንጠብቀውም። ሊያጠፋን የመጣ እንከላከላለን። ራስን መከላከል ያለ ነው። ራስን ከመከላከል ያለፈ በተራዘመ ጦርነት ሌላውን ለማጥፋት ማጥቃት ግን ትልቅ ኪሳራ የሚያስከፍል ብልሹ ስልት ነው። አጥቂውና ተጠቂው በውል ባልታወቀበት ሁኔታ ሁለቱም ወገን ሊያጠቃቸው የመጣ ከሚመስላቸው ወገን ጋር እየተዋጉ መኖር ግን ጥበብ የጎደለው የጥፋት ጎዳና ነው። አንዱ አንዱን አጠቃኝ ፣ ከምድረ ገፅ
ሊያጠፋኝ ነው ብሎ ምክኒያት እየሰጠ ፣ የምዋጋው ራሴን
ለመከላከል ለህልውናዬ ነው ብሎ በሚሟገትበት ሁኔታ በጦርነት መቀጠል ጥፋት እንጂ መፍትሄ አያመጣም።
ወደድንም ጠላንም አንድ ወገን ሌላውን ወገን እንዲያጠቃ ያደረገው የራሱ ስጋት አለበት። በእኛ አስተያየት ስጋቱ ተቀባይነት ይኑረውም አይኑረውም ቢያንስ ስጋቱ እኛን እንዲያጠቃን አስችሎታል። ማንም ሰው በትክክለኛ አእምሮ ሰላምን አይጠላም። ታዲያ ሌላው ወገን ከእኛ ጋር ጦርነት ውስጥ እንዲገባ ያደረገው ምክኒያት እንዳለ በትህትና ማመን እና መቀበል ብልህነት ነው። እንዲያው በደፈናው ሌላው ወገን ጦርነት ውስጥ እንዲገባ ምንም አይነት ምክኒያት የለውም ብሎ ማመን ራስን ማታለል ነው። ሌላው ወገን ጦርነት ውስጥ እንዲገባ ያደረገው ምክኒያት ምንድነው ብሎ በቅንነት መጠየቅ ለሰላም መፍትሄ አንድ እርምጃ ነው።
ሌላው ወገን ስጋት ውስጥ እንዲገባ ያደረገውን ነገር መጠየቅ ደግሞ ሌላው ወገን ጦርነት ውስጥ እንዲገባ ያደረገውን ነገር ተቀበልነው ፣ ስለትክክለኝነቱ ማረጋገጫ ሰጠንለት
፣ ከእርሱ ሃሳብ ጋር ተስማማን ማለት ደግሞ አይደለም። የሌላውን ወገን ስጋት መስማት ፣ በእኛ በኩል ስጋቱን ለመቀነስ ማድረግ የሚገባንን ነገር ሁሉ ማድረግ አብሮ በሰላም ለመኖር አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው።
ሌላው ወገን እንዲያጠቃን ያደረገውን እና ያጋጨንን ምክኒያት በቅንነት መስማት ተመሳሳይ ነገር ለወደፊት እንዳያጋጨን መነጋገር እና መደራደር ሌላውን መልሰን ገንዘባችን ማድረግ በስጋትና በጭንቀት ከመኖር ይገላግላል። ከሌላው ጋር መነጋገር እና መወያየት ወገናችን በጥላቻና በእልክ የሌላው መጠቀሚያ እንዳይሆን ያድነዋል።
በእልህና በአሳየዋለሁ ስሜት ጦርነቱን ማራዘም ሁለቱም ወገኖች ለእርዳታ ወደውጭ መንግስረታት እንዲዞሩ በማድረግ የጦር መሳሪያ የሚሸጡልንን አገሮች ከማበልፀግ ውጭ ለህዝቡ የሚጠቅመው ምንም ነገር የለምን። ለእርቅና ለድርድር አለመዘጋጀት በምድሪቱ መዋረድ የሚጠቀሙ አገሮች በሌላው ወገን ተጠቅመው አገሪቱን የውክልና የጦር ቀጠና እንዲያደርጉዋት መጋበዝ ነው። ከእኔ ይለፍ እርሱ ይጠቀም ብሎ አንዳንዱን ነገር መተው ግን ቢያንስ አንድነቱን የምንፈገልገው የአገራችን ሰው ወገናችን እንዲጠቀም ያደርገዋል፡፡ ከወገናችን ጋር ለመታረቅ እንቢ ማለት ግን ገንዘባችን ማድረግ ያለብንን ወገናችንን ጠለኻት ከማድረግ አልፎ ጠላታችንን ያበዛዋል፡፡
አንዳችን የአንዳችንን የጦር ችሎታ ለማሳየት አንድ አመት ከበቂ በላይ ነው። ሁለቱም ወገኖች አገርን ለማጎሳቆል የሚበቃ ሃይል እንዳላቸው ባለፉት አንድ አመት አስመስክረዋል። እርሱ ብቻ ሳይሆን ሁለቱም ወገኖች ከውጭ ሃይል ጋር ሆነው በአገሪቱ ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን አሰቃቂ የመከራ ጉልበት በግልጽ አሳይተዋል። አሁን ጥያቄው መሆን ያለበት ሃይል አላቸው የላቸውም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ሃይላቸውን መሞከር ሳይሆን ሃይላቸውንም ለጥፋት ሳይሆን ለሰላም እና ለልማት የመጠቀም ጉዳይ ላይ ነው። ሁለቱም ወገኖች የራሳቸው ጉልበት እንዳላቸው አይተናል እንመሰከርላቸዋለን።
ለፖለቲካ ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር ግጭት በግጭት እንደማይደመደም አንድ ቀን ድርድር ውስጥ እንደሚገቡ ሁለቱም ወገኖች ያውቁታል። ጥያቄው የፖለቲካ መሪዎች የሚደራደሩት በድህነቱ ወደ ወታደርነት የሚቀላቀለው ተራው ህዝብ አልቆ ወደ መሪዎቹና አዛዦቹ ደረጃ ሲደርስ መሆን ግን የለበትም። ጥፋት መቅረት ካለበት በተቻለ መጠንና ፍጥነት አንድ ተጨማሪ ሰው ሳይሞት አንድ ሰው ከሰላማዊ ኑሮው ሳይፈናቀል አሁን መሆን አለበት።
የህዝባቸው የሰላም ሃላፊነት እንዳለባቸው ሁለቱም ወገኖች በጠረጴዛ ዙሩያ ይቀመጡና ሃላፊነት እንደሚሰማቸው ሙሉ ሰዎች እንዲነጋገሩ ህዝቡ ይጠብቅባቸዋል።
ይህን ሁሉ ጊዜ አንዱ ሌላው ህሊና እንደሌለው ሊያሳየን ቢጥርም ሰው ህሊና እንዳለው በመነጋገር በመደራደር ብዙ ችግሮች ሊፈቱ እንደሚችሉ እናውቃለን። በዚህም በዚያም ያሉት መሪዎች እመራዋለው አገለግለዋለሁ የሚሉት ህዝብ ጉስቁልና ህሊናቸውን ይነካቸዋል። በዚህም በዚያም ወገን ያሉ መሪዎች የሚመሩት ህዝብ እየታዘበቸው ነው። ህዝብ በምጥ የሰላምን መምጣት በጉጉት እየጠበቀ ነው። የሚመሩት ህዝብ ሃላፊነት እንዳለባቸው መጠን በሚያስማማቸው ነገር ላይ በፍጥነት መስማማት ይጠበቅባቸዋል። በሁሉም ነገር ላይ ይስማማሉ ብሎ መጠበቅም ሞኝነት ነው። ነገር ግን ጥላቻን አስወግደው ተኩስ ካቆሙ እና በዋና ዋና ነገሮች ላይ ለመደራደር ከተቀመጡ ቢያንስ ህዝቡ ወደ ሰላማዊ ህይወቱ ከተመለሰ ትልቅ ድል ነው። በድርድሩ እርስ በእርሳቸው መስማማት ካልቻሉ ደግሞ ከዚህም በተጨማሪ ሁለቱም የሚያምኗቸው እና ለአደራዳሪነት የሚቀበሏቸው አስታራቂዎች ወገኖች በመካከል ገብተው እንዲደራደሩ ይረዷቸዋው።
እንዲታወቅበት የማይፈልገው የሚደብቀው ነገር ከሌላ በስተቀር ህዝብን በቅንነት እመራለሁ ለሚል ሰው ሁለቱም የሚያሸንፉበትን የሰላምን መንገድ ድርድርን እንደድል እንጂ እንደ ሽንፈት አያየውም። እኔነታቸውንና ትምክታቸውን ጥለው የሚሊዮኖች ሃላፊነት እንዳለባቸው ሰዎች ቢነጋገሩና ቢደራደሩ ታሪክ በመልካምነት ያስታውሳቸዋል እንጂ ማንም አይንቃቸውም።
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #እውነት #ዘር #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ትህትና #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #መሪ
Thursday, September 30, 2021
ግልፀ ደብዳቤ ለአገልጋይ ዮኒ
ግልፀ ደብዳቤ ለአገልጋይ ዮኒ
በቲክቶክ ላይ በብዙ ሰዎች የተካፈለ እና በከፍተኛ
ሁኔታ የተዘዋወረ ቪድዮ አየሁ፡፡ በቪድዮ ላይ አገልጋይ ዮኒ ፖለቲከኞችን ሚንስቶሮችን እንዴት እንደሚያስተምርና እንሚመክር ይናገራል፡፡
አገልጋይ ዮኒ ስለሙስና እና በስልጣንን ካለ አግባብ
ስለመጠቀም ሲናገር አትበሉም አልልም ትበላላችሁ በማለት ከአንድ የሃይማኖት መሪ የማይጠበቅ የብዙዎች መንፈሳዊ ንፅህና የሚያጎድል
እና ቅዱሳንን ለሰይጣን ጥቃት የሚያጋልጥ ክፉ ምክር ይመክራል፡፡
አትበሉም ብሎ መጀመር ሲኖርበት አትበሉም አልልም
በማለት ማንም ፖለቲከኛ ላይበላ እንደሚችል አምኖ ተቀብሎዋል፡፡ ሰው ፖለቲከኛ ሆኖ ንፁህ ሊሆን እንደሚችል በቃሉ ተስፋ ቆርጦዋል፡፡
አጋልጋይ ዮኒ ከንግግሩ ሰው ፖለቲከኛም የማይሰርቅ ክርስትያንም ሊሆን እንደሚችል አያምንም፡፡ ሰው በተለይም ፖለቲከኛ እና ባለስልጣን
በምድር ላይ ቅዱስ ሆኖ መኖር እንደማይችል ያለውን ተስፋ መቁረጥ በዚህ በተሸናፊነት ንግግሩ ያሳያል፡፡
ይባስ ብሎ ደግሞ "አትብሉ አልልም ብሉ" በማለት ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ጉባኤና ቪድዮ በሚለቀቅበት በመረጃ መረብ ፣ በማህበራዊ
ትስስር ገፆች የእግዚአብሄርን ቃል ለማያውቁ የአስተማሪን ቃል በእግዚአብሄር ቃል መዝነው ለማይቀበሉ ተከታዮች የሌብነት ፈቃድ ይሰጣል፡፡
ሲያስተምር የሚስሙት ሲደነግጡ ሳይሆን ሲስቁና ሲያጨበጭቡ ከጀርባ ይሰማል፡፡ በመረጃ መረብ ላይ በተለቀቀውም የቪድዮ ክሊፕ አስተያየት
ላይ እውነቱን ተናገረ ተብሎ ሲደነቅ አንብቤያለሁ፡፡
የመፅሃፍ ቅሱስ እውነት አትብሉ የሚለው ትእዛዝ
ነው እንጂ ብሉም ፣ ትንሽ ትንሽ ብሉም እንደመፅሃፍ ቅዱስ እውነት ግልፅ የስህተት ትምህርት ነው፡፡
ትንሽ ትንሽ ብሉ ማለት ምን ማለት ነው? ትንሽ
ትንሽ ብሉ ማለት ስንት ብሉ ማለት ነው? ትንሽ የሚለው ቃል ረቂቅና ሊመዘን የሚችል ስላይደለ አሻሚ ቃል ነው፡፡ ትንሽ የሚለው
ቃል ሰው ለስጋው የምኞት ሃጢያት አርነት እንዲሰጥ ከማድረግ ውጭ ሰው ራሱን በመግዛት ለእግዚአብሄር አላማ እንዲኖር አያበረታታም፡፡
ትንሽ ማለት ስንት ነው በመቶዎች በሺዎች በሚሊዮኖች ?
አገልጋይ ዮኒ ከአንድ የሃይማኖት መሪ የማይጠበቅ
የብዙዎች መንፈሳዊ ንፅህና የሚያጎድል ምክር ይመክራል፡፡
አገልጋይ ዮኒ በዚህ ንግግሩ እኔ ቅዱስ ነኝና
ቅዱሳን ሁኑ ከሚለው የእግዚአብሄር ቃል በተቃራኒ ያስተምራል፡፡ አገልጋይ ዮኒ በዚህ ትምህርቱ ራስን ከመግዛት ይልቅ ሰው በህይወቱ
ለሰይጣን ስፍራን እንዲሰጥ የሚያደርግ ጤናማ ያልሆነ ትምህርትን ያስተምራል፡፡
የእግዚአብሄር አገልጋይ የሆነው መጥምቁ ዮሃንስ
ስለባልስልጣኖች ሰልጣናቸውን ካለአግናባብ ሊጠቀሙ ስለሚችሉ ፖለቲከኞችና የአገር አስተዳዳሪዎች የመከረው ምክር አገልጋይ ዮኒ ከመከረው
ምክር ተቃራኒ ነው፡፡
ወታደሮ ደግሞ፣ “እኛስ
ምን እናድርግ?”
ብለው ጠየቁት።
እርሱም፣ “የማንንም ገንዘብ በግፍ
አትንጠቁ፤ ሰውንም
በሐሰት አትክሰሱ፤
ደመወዛችሁ ይብቃችሁ”
አላቸው። ሉቃስ
3:14
ይህ ማለት ግን አገልጋይ ዮኒ ያስተማራቸው ትምህርቶች
ሁሉ ስህተት ናቸው ማለት ግን አይደለም፡፡ ይህ ትምህርት ግን ንስሃንና መመለስን የሚጠይቅ እርሱም በህይወቱ ሊተገብረው የማይገባው
ሌሎችም ሊተገብሩት መምከር የሌለበት የስህተት ትምህርት መሆኑን አውቆ
በግልፅ ንስሃ መግባትና እንደመፅሃፍ ቅዱስ አስተምሮት አስተካክሎ ማስተማር አለበት፡፡
Tuesday, September 28, 2021
የሰይጣን መሳሪያ
የሰይጣን አላማው መስረቅ ማረድና ማጥፋት ነው፡፡ ሰይጣን ከመስረቅ ከማረድና ከማጥፋት ውጭ ሌላ ምንም አላማ የለውም፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
ይህንን የመስረቅ የማረድና የማጥፋት አላማውን
የሚያሳካው ደግሞ በውሸት ነው፡፡ ሰይጣን አለማማውን የሚያሳካው በመዋሸት እና በማታለል ነው፡፡
እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። የዮሐንስ ወንጌል 8፡44
ሰይጣን የራሱ ነገር የለውም፡፡ ሰይጣን የእግዚአብሄርን እውነትን አይቀበለም፡፡ ሰይጣን ከራሱ ሃሰትን ይናገራል፡፡
ሰይጣን ይዋሻል፡፡ ሰይጣን እውነትን ለውጦ ያቀርባል፡፡ ሰይጣን የሚያምኑትን ሰዎች ያታልላል፡፡
ሰይጣን ከመጀመሪያ ጀምሮ ውሸታም ነው፡፡ ከሰይጣን
ውሸት እንጂ ምንም ሌላ ነገር አይጠበቅም፡፡ ሰይጣን ተንኮለኛ ነው፡፡ የሰይጣን ሃይል ማታለል ስለሆነ ሰይጣን ሃሰቱን እውነት አስመስሎ
ለማቅረብ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡
ሰይጣን በተለይ በእግዚአብሄር ፊት ያለን ቦታ
ላይ ይዋሻል፡፡ እግዚአብሄር እንዴት በክብር እንደሚያየን በእግዚአብሄር ፊት ያለንን የክብር ቦታ ላይ በልባችን ጥርጥር ማስገባት
ከተሳካለት ሰይጣን ህይወታችንን በቀላሉ ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ እንደሚችል ያውቃል፡፡
ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3
ሰይጣን ዲያብሎስ በእግዚአብሄር ልጅነታችን ላይ
እንዲዋሽ ካልፈቀድንለት ግን ህይወታችንን የሚያጠቃበት ምንም ፈንታ እና ስፍራ ሊያገኝ አይችልም፡፡ ለሰይጣን በፍርሃት ስፍራን የምንሰጠው
ወይም በእምነት ስፍራን የምናሳጣው እኛው ራሳችን ነን፡፡
ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ወደ ኤፌሶን ሰዎች
4፡27
ሰይጣን ሔዋንን ያሳሳታት በእግዚአብሄር ፊት ባላት
ስልጣን በማንነትዋ ላይ በመዋሸት ነው፡፡ እግዚአብሄር በመልኩና በአምሳሉ ፈጥሮአት እያለ ልጅነትዋ ምንም እንዳይደለ ፣ ምንም ሊጠቅማት
እንደማይችል ፣ ከንቱ እንደሆነ እና የጎደላት ብዙ ነገር እንዳለ በውሸት በማሳመን በአመፃ ከእግዚአብሄር ክብር እንድትወድቅ አታለላት፡፡
እባብም ለሴቲቱ አላት፦ ሞትን አትሞቱም፤ ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ። ኦሪት ዘፍጥረት 3፡5
ዲያቢሎስ
ኢየሱስን በምድር ላይ ሲፈትነው የሰይጣን የውሸትና የንቀት ስልቱ ተመሳሳይ ነበር፡፡ ሰይጣን "የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ"
በሚለው የማናናቂያ እና የማጣጣያ የንቀት ንግግሩ በኢየሱስ ማንነት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ሞክሮዋል፡፡ የሰይጣን "የእግዚአብሔር
ልጅ ከሆንህ" የሚለው ንግግር ኢየሱስ በእግዚአብሄር ፊት ያለውን ልጅነት የሚያንቋሽሽ ምን ታመጣለህ? ዝም ብለህ ነው !
ምንም አይደለህም! ከማንም አትበልጥም! የሚል መልእክት ነበረው፡፡
ዲያብሎስም፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ይህን ድንጋይ፦ እንጀራ ሁን ብለህ እዘዝ አለው። የሉቃስ ወንጌል 4፡3
ኢየሱስ ግን የልጅነት ቦታውንና ስልጣኑን አጥብቆ
ያውቅ ስለነበር ለሰይጣን ማንቋሸሽ እና ማጣጣል አልተንበረከከም፡፡ ኢየሱስ የሰይጣንን የውሸት ንግግር በልቡ አላስተናገደውም፡፡
ኢየሱስ የሰይጣንን የማንቋሸሽ ንግግር ተቀብሎ እግዚአብሄር ከሰጠው አላማ ወጥቶ ለአንድም ሰአት ለሰይጣን ሃሳብ አልተገዛም፡፡ ኢየሱስ
የሰይጣንን የንቀትና የፍርሃት ንግግር ንቆ እግዚአብሄር የሰጠውን አላማ በድፍረት ፈፀመ፡፡
የሰይጣን የፍርሃት አላማ ሰውን ከአላማው ማስቆም
እንደመሆኑ መጠን የሰይጣን ፍርሃት እና ጥርጥር የሚጭር ንግግር ኢየሱስን ከአላማው እና ከእርምጃው አላቆመውም፡፡ የፍርሃት አላማ
እኛን ለምንም የማንጠቅም ፣ ሽባ ማድረግ እንደመሆኑ መጠን ኢየሱስን በፍርሃት ሽባ ሊያደርገው እና ከአላማው ሊያስቆመው አልቻለም፡፡
አሁንም ሰይጣን እኛን የሚፈትነን ልጅነታችንን
እና በልጅነታችን ያገኘነውን ነገር ጥርጣሬ ውስጥ በመክተት ነው፡፡ አሁንም የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ እስኪ ከዚህ ሁኔታ አምልጥ
፣ የእግዚአብሄ ልጅ ከሆንሽ ይህ ለምን ደረሰብሽ? የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ እንዲህ እና እንዲያ ለምን ሆነ? በማለት በእግዚአብሄር
ፊታ ያለንን ልጅነት ሊያጣጥል ይጥራል፡፡
እህህ ብለን ውሸቱ ከሰማነውና በማጣጣል ወጥመዱ
ውስጥ ከገባንለት የእግዚአብሄር ልጅ አይደላችሁም ፣ ዝም ብላችሁ ነው ፣ ከእኔ ሃይል አታመልጡም ብሎ ሊያሳምነን ይፈልጋል፡፡
ሰይጣን የህይወት ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን ውሸታም
ነው፡፡ ሰይጣን የሚጠቀመው በማታለል ነው፡፡ በህይወታችን አሸናፊ ለመሆን ከሰይጣን ንግግር በላይ እና ከሁኔታ በላይ የእግዚአብሄርን
ቃል ልናምን ይገባናል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ዲያቢሎስ
#ጠላት #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ሐሰት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ውሸት #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #ማታለል #የተሸነፈ #በረከት #ትግስት
#መሪ