Popular Posts

Wednesday, July 29, 2020

1


አንድ ፡ ወዳጅ (And Wedaj) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
<Kefa Mideksa‎ |
አንድ ፡ ወዳጅ (4x) ፡ አለኝ
ለእኔ ፡ የሞተልኝ (4x)

ቅጣቴን ፡ የተቀጣህልኝ
አበሳዬን ፡ ከእኔ ፡ ወሰድክልኝ (2x)
ጌታ ፡ ተባረክልኝ
ኢየሱስ ፡ ተባረክልኝ
ጌታ ፡ ተባረክልኝ (2x)

ሙግቴን ፡ ተሟግቶ ፡ አሸንፎልኛል
ጠላቴ ፡ እንዳይከሰኝ ፡ ነጻ ፡ ነህ ፡ ብሎኛል
ይህን ፡ ወዳጄን ፡ ወዳጄ ፡ ነህ ፡ ያልኩት
ከማንም ፡ አብልጬ ፡ በልቤ ፡ የሾምኩት

አዝ፦ ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው
መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው
ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው
መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው
እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (2x)
እርሱ ፡ ጌታዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ነው (2x)

በምክሩ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ነፍስን ፡ ይመልሳል
ከወዳጅ ፡ አብልጦ ፡ ወደ ፡ ልብ ፡ ይጠጋል
ደብቆ ፡ የያዘኝ ፡ እንዳልሆን ፡ የሌላ
የቅርቤ ፡ የምለው ፡ ማነው ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ

አዝ፦ ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው
መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው
ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው
መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው
እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (2x)
እርሱ ፡ ጌታዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ነው (2x)

Saturday, July 25, 2020

Man is created for love

Man is created for love

God Is Love. Man is created by the God who is love.

Whoever does not love does not know God, because God is love. 1 John 4:8

God created man to be loved and to love. Man is created to love and to be loved. Man is designed for the purpose of giving and receiving love.

And man is primarily created to receive God's love and to love God.

Love the Lord your God with all your heart and with all your soul and with all your mind and with all your strength. Mark 12:30

If man fails to receiving the love of God, he will not succeed in every other love life.

If man doesn't understand God's love towards him, he doesn't understand the love to himself and to others.

If a man knows how to receive love from God, He is able to love God back and to love others.

A man who doesn't know how to receive love from God,  isn't able to love God and others.

Any problem of receiving and giving love can be traced back to the problem of receiving God's love.

Understanding the love of God is the source of understanding the love for self and others.

And hope does not put us to shame, because God’s love has been poured out into our hearts through the Holy Spirit, who has been given to us. Romans 5:5

#Love #god #Jesus #Church #Truth #Abiydinsa #Abiywakumadinsa #Apostleabiy #Abiywakuma #Wordofgod #Bible 

ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:8-9


Sunday, July 12, 2020

Friday, July 10, 2020

ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ። የሐዋርያት ሥራ 24:16


አመሰግናለሁ (Amesegenalehu) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል



የእግዚአብሔር ቸርነት ምህረቱ ከቦኝ ነው ዛሬ ላይ መቆሜ አሄ
ትንፋሼን መንገዴን በእጆቹ የያዘው ሆኖልኝ አቅሜ ሄሄ
ወራት ተቆጠሩ አመታት አለፉ ዛሬም ዘምራለሁ አሄ
በሕይወት እንድኖር ስለፈቀደልኝ አመሰግናለሁ ሆሆ

አቤት አቤት የእግዚአብሔር ቸርነት የእግዚአብሔር ምህረት
አቆመኝ እኔም ልስገድለት
እጄን ይዞኝ አምላኬ ወዶኛል ጌታ ራርቶልኛል
ሳመልከው እጅግ ደስ ይለኛል
ሳመልከው እጅግ ደስ ይለኛል (4x)

Thursday, July 9, 2020

የመሰረታዊ ፍላጎት እምነት



ብዙ ሰው ስለብዙ ነገር እምነት እንዳለው ይናገራል፡፡ ሌላው ሰው ደግሞ ስለብዙ ነገሮች እምነት እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ እንዲሁ ሌላው ደግሞ ስለ ትልልቅ ነገሮች እምነት እንዲኖረው ይመኛል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስን አምኖ ከመቀበል ውጭ በጣም አስፈላጊው እምነት ስለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን ማመን ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ስለብዙ ነገር እምነት የሚያስፈልጋቸው ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ከደህንነት ቀጥሎ በጣም የሚያስፈልጋቸው እምነት የመሰረታዊ ፍላጎት እምነት ነው፡፡
እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 632-33
ብዙ ሰዎች ስለብዙ ነገር እምነት እንዲኖራቸው ቢፈልጉም በቅርበት ፍላጎታቸው ቢጣራ በመሰረታዊ ፍላጎት መቸገር አለመፈለግ ነው፡፡ ስለትልልቅ ነገሮች እምነት እንዲኖራቸው የሚፈልጉት ሰዎች ፍላጎታቸው በቅርብ ቢታይ ስለትልልቅ ነገር ማን የሚፈልጉት በተዘዋዋሪ ለመሰረታዊ ፍላጎት እንዲረዳቸው መቸገርን ስለሚፈሩ ነው፡፡ ሰው አሁን ከሚጠቀምበት በላይ ብዙ ውድ ሃብት ማከማቸት የሚፈልገው ነገ እንዳይቸገር ከመፍራት ሊሆን ይችላል፡፡
ሰው ምንም አይነት እምነት አለኝ ቢል ነገር ግን ስለ ነገ ኑሮው ስለ መሰረታዊ ፍላጎቱ እግዚአብሄርን ካላመነ እምነት የለውም፡፡ ሰው ስለመሰረታዊ ፍላጎት ካመነ ደግሞ እምነቱ መሰረት አለው፡፡
ከደህንነት ቀጥሎ ስለምንንም ነገር እምነት ከማጣት በላይ ሰውን የሚጎዳው የሚያስጨንቀውና የሚያስፈራው ስለመሰረታዊ ፍለጋት እምነት ማጣት ነው፡፡
በእሾህ መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው፥ የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል ቃሉን ያንቃል፥ የማያፈራም ይሆናል። የማቴዎስ ወንጌል 13፡22
ስለመሰረታዊ ፍላጎት እምነት የሌለው ሰው በነፃነት ለእግዚአብሄር ሊኖር እግዚብሄርን ሊያገልግል አይችልም፡፡ ስለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን ያመን ሰው እግዚአብሄር በወደደው መልኩ ሊጠቀምበት የሚችል ከፍርሃትና ከጭንቀት ነፃ የወጣ ሰው ነው፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #አትጨነቁ #ቅድሚያ #ምንእንበላለን #ምንእንጠጣለን #ምንእንለብሳለን #መሰረታዊፍላጎት #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ሰለሞን #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ድንግል #ማርያም #ኦርቶዶክስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

New Ethiopian Mezmur by Abush Menor (አቡሽ መኖር) በእግዚአብሔር ሰላም #በእግዚአብሔርሰላም...

Sunday, July 5, 2020

ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ የዮሐንስ ወንጌል 14:1


የእርሱን አሳብ አንስተውም




በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና። 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 211
እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚሰራው በፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚገኘው በፍቅር መካከል ነው፡፡
ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1 የዮሐንስ መልእክት 48
በተቃራኒው ሰይጣን ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ይመጣል፡፡ ሰይጣን ከመስረቅ ከማረድና ከማጥፋት ውጭ ሌላ አሳብ የለውም፡፡ ይህንን አላማውን የሚያስፈፅመው በጥላቻ ነው፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 1010
ይቅር አለማለት ምሬትና ጥላቻ የሰይጣን ለም መሬት ነው፡፡ ሰይጣን በጥላቻ ልብ ውስጥ ምንም ክፉ ነገር ቢዘራ ይበቅልለታል፡፡ በሰው ውስጥ ጥላቻን ማድረግ ከቻለ ሰውን ይሰርቃል ያርዳል ያጠፋል፡፡
ሰይጣን ሰውን ሲሰረቅ ሲያርድና ሲያጠፋ አላማው ይህንን አላማ በስፋት ማከናወን ነው፡፡ የተሰረቀው ሰው ለሌላውን ሰው ይጠላል፡፡
ሰይጣን ሲገድል የአንዱን ግድያ አሳቦ አንዱ ሌላውን እንዲጠላውና ፈረሱ እንዲሆንለት ያደርጋል፡፡ የሰይጣንን ጥላቻ የሚያስተናግድ ሰው ሰይጣን ወደፈለገው ቦታ የሚጋልበው የሰይጣን ፈረስ ነው፡፡
እናንተ ግን ይቅር የምትሉትን እኔ ደግሞ ይቅር እለዋለሁ፤ እኔም ይቅር ካልሁ፥ ይቅር ያልሁትን ስለ እናንተ በክርስቶስ ፊት ይቅር ብዬአለሁ፥ በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና። 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 210-11
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ዲያቢሎስ #ጠላት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ማታለል #የተሸነፈ #በረከት #ትግስት #መሪ