I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
በአለማችን ላይ እውነተኛ ደቀመዛሙርቶች አሉ፡፡ የስም ብቻ ደቀመዛሙርቶች ደግሞ አሉ፡፡ እውነተኛ ደቀመዝሙር የሚያደርገን ምን እንደሆነ ማወቅ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡ የእውነተኛ ደቀመዝሙርነት መንገድ ላይ መሆናችንን ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር ፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ...
-
https://youtu.be/VhF0pSsp14I በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን
-
Live soberly and be vigilant, for the devil, who is not your partner, prowls around like a roaring lion looking for someone to devour. Re...
-
ነቢይ የእግዚአብሄር አፍ ነው፡፡ ነቢይ ከለአግዚአብሄር ሰምቶ የሚናገር ነው፡፡ ነቢይ የእግዚእብህር በልቡና ያለውን ተረድቶ ለህዝቡ የሚገልፅ ነው፡፡ በድሮ ዘመን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄር ነቢይን በዚህ በእኛ ዘመን ...
-
ተጠማው እልውናህን መገኘትህን ጌታ ድምጽህን መዓዛ ግርማህን አልፈልግም ኖረ ኖረ ኖረ ሞተ አልፈልግም መሆን በምድር የታመነ መንፈስክን ይዞ ይዞ ሚገሰግስ ለተጠማው ደርሶ የልብህን የሚያደር...
-
Bait your hook an' keep a- tryin '-- Keep a-goin '! When the weather kills your crop, Keep a-goin '! Though 'tis...
-
የወርቅ ቀለበት በእርያ አፍንጫ እንደ ሆነ፥ ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴትም እንዲሁ ናት። መጽሐፈ ምሳሌ 11፡22 የኛውም ወርቅ እርያን አንደማያሳምረው ሁሉ የትኛውም የውጭ ውበት የውስጡን ሰውን አያ...
-
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠ...
-
በነጻነት ሕግ ፍርድን ይቀበሉ ዘንድ እንዳላቸው ሰዎች እንዲህ ተናገሩ፥ እንዲህም አድርጉ። የያዕቆብ መልእክት 2፡ 12 በክርስቶስ ከሃጢያት እስራትና ፍርድ ነፃ ወጥተናል፡፡ ነገር ግን ነፃነት የሚመጣ...
Monday, May 13, 2019
የደስተኝነት ምርጫ
በህይወት ደስተኛ መሆን የእድል ጉዳይ ሳይሆን የምርጫ ጉዳይ ነው:: ሰው ሁሉ ደስተኛ መሆን ይፈልጋል:: ነገር ግን ሰው ሁሉ ደስተኛ የሚያደርገውንነገር አይመርጥም:: እንዳንድ ሰው ደስተኛ ለመሆን ቢፈልግም ደስተኛ የሚያደርጉትን ሳይሆን ደስተኛ የማያደጉትን ነገሮች ስለሚመርጥ ደስተኛ ሳይሆን ጊዜውን ያባክናል::
ክፉ ሀዘን ጉልበትን ያደክማል:: ክፉ ሀዘን የኑሮ መነሳሳትን ይገድለዋል::
እርሱም፡— ሂዱ፥ የሰባውንም ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያም ላልተዘጋጀላቸው እድል ፈንታቸውን ስደዱ፤ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ፡ አላቸው። መጽሐፈ ነህምያ 8:10
ደስተኝነት ለመኖር ለመስራትና ወደህይወት ግባችን ለመድረስ ጉልበት ይሰጠናል::
በህይወት ደስተኛ የማያደርገንን ነገሮች እስካልመረጥን ድረስ ደስተኛ መሆናችን አይቀርም::
ደስተኛ የማያደርጉ ሀሳቦች
1. ራስን ከሌላ ሰው ጋር ማፎካከር
ደስተኛ ላለመሆን አቋራጩ መንገድ በህይወት የተለያየ የህይወት አላማና ስጦታ ያላቸውን ሰዎች ለማወዳደርና ለማበላለጥ መሞከር ነው::
ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። 2ኛ ቆሮንቶስ 10:12
2. ያለፈን ህይወት በፀፀት ለማስተካከል መሞከር
ያለፈ ህይወት አልፎዋል:: ስላለፈ ህይወት መፀፀት ዛሬን መግደል ነው:: ስላለፈ ህይወት መፀፀት ከዛሬ ትላንት ይሻል ነበር ብሎ ዛሬን ማናናቅ ነው::
3. የሌለን ነገር ላይ ማተኮር
የሌለን ነገር ላይ ማተኮር ያለንን ነገር በአግባቡ እንዳንጠቀምበት ያደርገናል:: የሌለን ነገር ላይ ማተኮር ያለንን እንዳናከብረውና እንዳንንቀው ያደርገናል:: የሌለን ነገር እንደማያስፈልገን ምንም ማረጋገጫ የለንም::
4. ያልደረስንበት ደረጃ ላይ ማተኮር
ሁላችንም ህልሞች አሉን:: ነገር ግን አሁን አንዳንዱ ህልማችን እውን ሆኖ እየኖርነው አይደለም ማለት አይደለም:: ከዚህ በፊት ምንም ሆኖልን እንደማያውቅ ምንም አከናውነን እንደማናውቅ የነገ ግባችን ላይ ከመጠን በላይ ማተኮር ደስተኛ ላለመሆን መምረጥ ነው::
5. ከጌታ ውጭ ማተኮር
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄርና ከእግዚአብሄር ጋር እንዲኖር ነው:: ሰው ግን እግዚአብሄርን ካላሰበ ደስተኛ መሆን ያቅተዋል:: ብዙ ደስ የማያሰኙ ነገሮች በዙሪያችን እያሉ በጌታ ደስ መሰኘት ይቻላል::
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ወደ ፊልጵስዩስ 4:4
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment