Popular Posts

Follow by Email

Saturday, November 10, 2018

ፍቅር ገደብ ያስፈልገዋል


ኢትዮጰያና የኤርትራ መለያየት ያልነበረባቸው ህዝቦች ነበሩ፡፡ አሁንም ኢትዮጰያና የኤርትራ ግንኙነት መታደስና መጠናከር ሁለቱንም ህዝቦች ደስ ሊያሰኝ ይገባል፡፡ ሁለቱ አገሮት በፖለቲካ በኢኮኖሚያ በማህበራዊው ዘርፍ እጅ ለእጅ ተያይዘው ቢሰሩ በግላቸው ከሚሮጡት በላይ ፍሬያማ ይሆናሉ፡፡
ነገር ግን ማንኛውም ግንኙነት ደግሞ ገደብ ሊኖረው ይገባል፡፡ ማንኛውም ግንኙነት በመርህ ላይ የተመሰረተ መጀመሪያውና መጨረሻው የሚታወቅ ሊሆን ይገባል፡፡ ማንኛውም ግንኙነት ቅድሚያ የሚሰጠውና የማይሰጠው ነገር ሊኖር ይገባል፡፡
ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ሰሞኑን የኤትርራው ፕሬዝዳንት የአማራ ክልል ጉብኝት ወቅት በንንግግራቸው ላይ ያነሱት ነጥብ ነው፡፡ 
በንግግራቸው የአማራ ህዝብ ወዳጅ እንደሆኑ ነገር ግን ችግር የፈጠረባቸው ህወአት መሆኑን በንግግራቸው ገልፀዋል፡፡ ይህ አሁን አገሪትዋ እየተከተለችው ላለችው የህዝቦች መቀራረብ እርቅና ሰላም የሚሰጠው ምንም ፋይዳ የሌለና እንዲያውም እንቅፋት የሚሆን ንግግር ነው፡፡
ኢትዮጲያና ኤርትራ ሁለት የተለያዩ አገሮች ናቸው፡፡ የሚያደርጓቸው ግንኙነቶች በአገር ደረጃ የተወሰነ ግንኙነቶች መሆን አለባቸው፡፡ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የአማራ ክልል ጉብኝት በፌደራል መንግስቱ በኩል የተደረገ ከሆነ ምንም ችግር የለውም፡፡ ነገር ግን የፕሬዝዳንት አፈወቀርቂ ንግግር በመንግስታት ደረጃ ከሚደረግ የጉብኝት ንግግር የዘለለ ነበር፡፡
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በንግግራቸው ህወአትን በመቃወም "ተከፍሎ የማያልቅ ግፍ የፈፀመብን ህወሃት ነዉ" ብለው የተናገሩን እውነት ቢሆንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ ላለው ለህዝቦች መቀራረብ እርቅና ሰላም የማይጠቅም ብሎም የሚጎዳ ንግግር ነው፡፡ 
ኢትዮጲያን የሚመራው የኢሃዲግ መንግስት ነው፡፡ ህወአት ደግሞ የኢህአዲግ አባል ድርጅት ነው፡፡ ህወአት በኢህአዲግ በኩል ኢትዮጲያን እየመራ ያለ ገዢ ፓርቲ ነው፡፡
ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጲያ መንግስት ለጉብኝት ተጋብዘው የኢትዮጲያን መንግስት እየመራ ያለውን የገዚውን ፓርቲ የኢህአዲግን አባል ድርጅት መተቸት የሚገባቸው አይመስለኝም፡፡ የኢትዮጲያን መንግስት እያስተዳደረ ያለውን የኢሃዲግን አንዱን አባል ድርጅት ሲኮንኑ  አሁን ላለንበት የሰላም የእርቅና የመቀራረብ ደረጃ ስለማይመጥን ማስተካከያ ሊሰጥበት ይገባል፡፡ 
ይህ አይነት በህወአትና በኤአግ /በሻብያ/ መካከል የነበረው ድንበርንና ወስንን ያልለየ ፈር የለቀቀ ግንኙነት ለኢትዮ ኤርትራ ጦርነት መነሳት አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ አሁንም የሁለቱ አገሮች ግንነት እንደጉርብትና ድንበት ሊበጅለት ይገባል፡፡
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ቢሆኑ ከኢትዮጲያ ጋር ያለላው ግንኙነት ድንበሩን ያላለፈ ሊሆን ይገባዋል፡፡ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ በኢትዮጲያ የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ባይገቡ ለሚመለከታቸው ክልሎችና የፖለቲካ ድርጅቶች ቢተዉት ይመረጣል፡፡
አሁን ኢትዮጲያና ኤርትራ የተለያዩ አገሮች ናቸው፡፡ ግንኙነታቸውም የጉርብትና በሁለት አገሮች መካካል ያለ ግንኙነት ሊሆን ይገባዋል፡
የአማራ ክልላዊ መንግስት ከኤርትራ ሃገር ጋር ካለው ግንኙነት ይልቅ በኢትዮጲያ ውስጥ ያለውን ከትግራይ መንግስትና የትግራይን መንግስትን ከሚመራው ከህወአት ጋር ያለው ግንኙነት ይበልጥበታል፡፡ የአማራ ክልላዊ መንግስት ከትግራይ ክልላዊ መንግስት ጋር የሚያጋጨውን ነገር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቢጥር ይመረጣል፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግስት አመራሮችና የአማራ ክልላዊ መንግስት አመራሮች ለመነጋገርና ለመተማመን የሌላ አገር መሪ በጉዳያቸው ውስጥ ጣልቃ እንዲገባ አያስፈልጋቸውም፡፡ 
የአማራ ክልላዊ መንግስትና የትግራው ክልላዊ መንግስታት በክልልም የሚዋሰኑ በመሆናቸው ያለባቸውን ማንኛውም ችግር በእርጋታ ቢፈቱ ይመረጣል፡፡ ሁለቱ ክልሎች እና ሁለቱ ፓርቲዎች ካለማንም የውጭ ጣልቃ ገብነት በመቀራረብ ለሰላምና ለአብሮነት መስራታቸው ለአገሪቱ አንድነትና እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
ፕሬዝዳንት ኢሳያስም ቢሆኑ በኢትዮጲያ ውስጥ ባሉ ክልሎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ያን ያህል ጣልቃ እንዲገቡ በፌደራል መንግስቱ በኩል ገደብ ሊበጅላቸው ይገባል፡፡ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአጠቃላይ የአገር ጉዳዮች ላይ የአገር ለአገር ግንኙነት ብቻ ላይ ማተኮት ይኖርባቸዋል፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ኤርትራ #ሰላም #እርቅ #ክልል #ህወአት #ፍትህ #ፍርድ #አናሳ #አብላጫ #ዲሞክራሲ #ጭቆና #እምባገነን #ሰብአዊመብት #ገደብ #ወሰን #ነገ #ትላንት #መሪ#ድሃ  #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment