Popular Posts

Saturday, September 5, 2026

የጩኸት ህይወት

መዝሙር 19:1 ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።

መዝሙር 19:2 ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።

መዝሙር 19:3 ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።

መዝሙር 19:4 ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።

ተፈጥሮ በስራው ካለቃል እና ንግግር በስራው ብቻ ስለእግዚአብሔር ክብር ይናገራሉ። 

አንድ አባባል አለ። ወንጌልን ስበክ አስፈላጊ ከሆነ ቃልን ተጠቀም። 

በቀዳሚነት ወንጌልን የሚሰብው ህይወታችን ነው። 

እግዚአብሔርን የመፍራት ህይወት ሲኖረን በህይወታችን ብቻ ሌሎች እግዚአብሔርን እንዲፈሩ እናስገድዳለን እናስፈራራለን። 

መልካም ስራችን ስለእግዚአብሔር መልካምነት በጩኸት ይናገራል። 

ማቴዎስ 5:16 መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።

የሚያስችለው ሀይል የእግዚአብሔር ፀጋ በህይወታችን ሲገለጥ ሰዎችን የሚቀሰቅስ ሀያል ጩኸት ነው። 

ንፁህ ህይወት ከሩቅ የሚሰማ ጬኸት ነው። 

1 ጴጥሮስ 3:1-2 እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው።

1 ጴጥሮስ 3:3 ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፥

1 ጴጥሮስ 3:4 ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

No comments:

Post a Comment