ጸሎት ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ነው። ጸሎት ሊደረግ የሚችለው ከእግዚአብሄር ጋር በመግባባት ብቻ ነው። ጸሎት የሚሰምረው
እንደ እግዚአብሄር አሳብ ስንጸልይ ብቻ ነው።
በአጠቃላይ ለእግዚአብሄር ያለን አመለካከት የጸሎታችንን ውጤታማነት ይወስናል።
ጸሎት ፍሬያማ የሚሆነው ለእግዚአብሄር የአምላክነት ስልጣን እውቅና በሰጠን መጠን ብቻ ነው። ጸሎት የሚሰምረው ከምስጋና
ልብ ሲወጣ ብቻ ነው።
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡17-18
ወደ እግዚአብሄር በጸሎት የመቅረብ አንደኛው ደንብ ወይም አሰራር
ምስጋና ነው።
ልመናና ጸሎት ምልጃም መቅረብ ያለበት በምስጋና ብቻ ነው።
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት
ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ
ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት #ሀበሻ #ምስጋና