I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱ...
-
ፍቅር አስደናቂ ነው፡፡ በተለይ ፍቅር ሁሉን ያምናል የሚለውን ቃል ሳሰላስል ነበር ያመሸሁት፡፡ ይህን ቃል ሳሰላስል ጌታ የሰጠኝን መረዳት አብሬያችሁ ልካፈል ወደድኩ፡፡ ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡ 1ኛ ቆሮንጦስ ...
-
መጠበቅ ሁል ጊዜ ለስጋ አይመችም፡፡ ስጋ የሚፈልገው ሁሉ ነገር ወዲያው እንዲሆንለት ነው፡፡ ረጋ ብሎ ጠብቆ የሚሆንን ነገር የሚመርጠው ጥቅሙን የሚረዳ የበሰለ ሰው ብቻ ነው፡፡ ተፈጥሮአዊው ሰው ቢች...
-
Our lives should be lived with the intent of fulfilling God's purpose for us, rather than simply existing. That is the final conclusio...
-
በክርስትና ህይወት ዘመኔ ድንበርን እንደማለፍና ልክን እንዳለማወቅ የክርስቲያንን ሰላም የሚረብሽ ነገር አላየሁም፡፡ ክርስትና የእግዚአብሄርና የሰው ድርሻ ያለበት ስራ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚሰራው ነገር አለ፡፡ ሰው...
-
በነጻነት ሕግ ፍርድን ይቀበሉ ዘንድ እንዳላቸው ሰዎች እንዲህ ተናገሩ፥ እንዲህም አድርጉ። የያዕቆብ መልእክት 2፡ 12 በክርስቶስ ከሃጢያት እስራትና ፍርድ ነፃ ወጥተናል፡፡ ነገር ግን ነፃነት የሚመጣ...
-
በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካ...
-
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠ...
-
ክርስቲያኖች ኢየሱስ ጌታ ነው በሚለው ንግግራቸው ይታወቃሉ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው በሚለው የሶስት ቃላት አረፍተ ነገር ውስጥ እጅግ የተጠቀጠቁ ትርጉሞች ይገኙበታል፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው ሲባል 1. ኢየሱስ በሰማይ ...
-
ሰው በህይወት እንዲከናወንለት የሚያስፈልገውን ነገር ማድረግ አለበት እንጂ ሰው በድንገት እንደ እድል አይከናወንለትም፡፡ በህይወይት ለመከናወን ራዕይ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ ራዕይ የሌለው ሰው የትም አይ...
Sunday, May 31, 2020
የነፍስ ብቻ ሳይሆን የስጋ ፈውስ ያስፈልገናል
Friday, May 29, 2020
Thursday, May 28, 2020
Tuesday, May 26, 2020
ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53
1፤ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
2፤ በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
3፤ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።
4፤ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
5፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
6፤ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
7፤ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
8፤ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
9፤ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገንበትም ነበር።
10፤ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈከደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
11፤ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሰከማል።
12፤ ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
Monday, May 25, 2020
የደስታ ያለህ
ክርስቲያናዊ ደስታን አፈላለግ በሚቀጥሉት አምስት እምነቶች ላይ የተገነባ የህይወት መረዳት ነው፡፡
l. ደስተኛ ለመሆን መጓጓት አለም አቀፋዊ ሁለንተናዊ የሰዎች ምኞት ነው፡፡ ደስተኛ ለመሆን የመመኘት ልምምድ መልካም እና ምንም ክፋት የሌለበት ነገር ነው፡፡
2. መጥፎ ስሜት ይመስል ደስተኛ የመሆን ምኞታችንን ለመካድ ወይም ለመቃወም በፍጹም መሞከር የለብንም፡፡
ይልቁን ጥልቅ እና በጣም ዘላቂ እርካታን ለማግኘት ይህንን ምኞት ማጠንከር እና ማዳበር አለብን፡፡
3. እጅግ ጥልቅ እና ዘላቂ ደስታ የሚገኘው በእግዚአብሄር ውስጥ ብቻ ነው፡፡
4. በእግዚአብሔር የምናገኘው ደስታ ከሌሎች ጋር በፍቅር ሲጋራ ወደ ደስታ ፍጻሜ ይደርሳል፡፡
5. የራሳችንን ደስታ ለማሳደድን እስከሞከርን
ጊዜ ድረስ ግን እግዚአብሄርን ማክበርና ሰውን መውደድ ያቅተናል፡፡
በሌላ አነጋገር የሰው ልጅ ዋናው ፍፃሜ በእግዚአብሄር
ለዘላለም ደስ በመሰኘት እርሱን ማክበር ነው፡፡
From the Book Desiring God by
John Piper Page 16.
Tuesday, May 19, 2020
Wednesday, May 13, 2020
ስጡ
ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል። የሉቃስ ወንጌል 6፡38
ይህ የኢየሱስ ንግግር ስለመስጠት እንጂ ስለ መቀበል
የተደረገ ንግግር አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ይህን ክፍል ስለመቀበል ይሰብኩታል፡፡ የዚህ የመስጠት ትምህርት አላማ ግን መስጠት
እንጂ በፍፁም መቀበል አይደለም፡፡
ሰው ሲሰጥ ወደ አእምሮው የሚመጣ ጥያቄ አለ፡፡
ስሰጥ እኔስ ቢጎድልብኝ የሚል ጥያቄ በሁላችንም አእምሮ ውስጥ ይመላለሳል፡፡
ሰጥቼ እኔስ ቢጎድልብኝ የሚለው ጥያቄ የሚፈጠርብን
ምክኒያት ገንዘብ ጊዜያዊም ቢሆን የመተማመን ስሜትን ስለሚሰጠን ነው፡፡
በአጠቃላይ አለምን የሚያንቀሳቅሰው የእግዚአብሄር
ፍቅር ወይም የገንዘብ ማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ሰው እንዳያጣ ብዙ ነገሮችን ያደርጋል፡፡
እንግዲህ፦ ምን እንበላለን?
ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። የማቴዎስ ወንጌል 6፡31-32
ሰው ገንዘቡን ለመስጠት የሚገዳደረው ምክኒያት
ገንዘብ የመተማመን ስሜትን በሰው ውስጥ ስለሚፈጥር ነው፡፡
ታዲያ ገንዘባችንን ስንሰጥ የምንሰጠው መተማመኛችንን
ነው፡፡ ገንዘባችንን ለመስጠት ከገንዘብ በላይ የምንተማመንበት እግዚአብሄርን ማመን ይጠይቃል፡፡ ገንዘብ ለመስጠት ከሚታየው ያለፈ
የእግዚአብሄርን መንግስት አሰራር በእምነት አይን ማየት ይጠይቃል፡፡ ገንዘብን ለመስጠት የእግዚአብሄርን ቃል ማመን ይጠይቃል፡፡
ለዘሪ ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል፥ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፤ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡10
ስጡ ብሎ ኢየሱስ ይሰጣችኋል ያለበት ምክኒያት
በሰው ውስጥ የሚነሳውን ሰጥቼ ቢጎድልብኝስ? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው፡፡ ስጡ ብሎ መልሱ ባጣስ ለሚለው ጥያቄ መልሱ ስለሰጣችሁ
አይጎድልባችሁም የሚለው ነው፡፡ ስለሰጣችሁ አታጡም ስለሰጣችሁ አትከስሩም፡፡
ይህንም እላለሁ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡6
ስትሰጡ ይሰጣችሁዋል፡፡ ስትሰጡ ይጨመርላችሁዋል፡፡
ስትሰጡ ይበልጥ ይሰጣችሁዋል፡፡
ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ
ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል። የሉቃስ ወንጌል 6፡38
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት
#መደገፍ #ሰንበት
#መዝራት #ማጨድ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ
#መንፈስቅዱስ #ምህረት
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ







