እግዚአብሄር
ቸር ነው፡፡ እግዚአብሄር መልካም አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በልግስና በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሳይሰስት ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ፈጠረው፡፡
እግዚአብሔርም
አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26-27
እግዚአብሄር
የዘላለም ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሄር የዘላለም ገዢ ነው፡፡
እግዚአብሔር
ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና። መዝሙረ ዳዊት 47፡2
እግዚአብሄር
ሰውን ሲፈጥር እንደ እርሱ አድርጎ ምድርን እንዲገዛና እንዲያስተዳድር ነው፡፡
እግዚአብሔርም
አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26-27
እግዚአብሄር
ሁሉን ይችላል፡፡
ለእግዚአብሔር
የሚሳነው ነገር የለምና። የሉቃስ ወንጌል 1፡37
ለእግዚአብሄር
የሚያቅተው ነገር የለም፡፡
እነሆ፥
እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ በውኑ እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን? ትንቢተ ኤርምያስ 32፡27
እምነት
የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል በመስማት ነው፡፡ እምነት የሚመጣው ስለአንድ ነገር የእግዚአብሄር አላማ በመረዳት ነው፡፡ እምነት የሚመጣው ስላለንበርት ሁኔታ የእግዚአብሄር ፈቃድ በመረዳት ነው፡፡
እንግዲያስ
እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡17
የእግፍዚአበሄር
ቃል በመስማት እምነትን ላገኘ ሰው የሚሳነው ነገር የለም፡፡
ሰው
የእግዚአብሄርን ቃል ቢሰማ የማይቻለው ነገር አይኖርም፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡
ኢየሱስም፦
ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። የማርቆስ ወንጌል 9፡23
የእግዚአብሄርን
ፈቃድ ስንፈፅም ምንም ነገር ፊታችን እንዲቆም እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄርን በቃሉ ስንሰማ በህይወታችን የእግዚአብሄርን አላማ ከመፈፀም ምንም አያቆመንም፡፡ እግዚአብሄር የማይችለው ነገር እንደሌለ ሁሉ እግዚአብሄርን ስናምን የሚሳነን ነገር አይኖርም፡፡ እግዚአብሄር በእምነት የማንችለው ነገር እንዳይኖር ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሄር
የፈጠረን እርሱ አላማውን ለማስፈፀም የሚከለክለው የሚያግደው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የእግዚአብሄር ፈቃድ በምድር ላይ እንድናስፈፅም በእምነት የሚሳነን ነገር እንዳይኖር አድርጎ ነው፡፡
የእግዚአብሄርን
ፈቃድ ስንፈፅም በህይወት በዘመናችን ሁሉ በፊታችን የሚቆም ነገር እንዳይኖር አድርጎ አሸናፊ አድርጎ ፈጥሮናል፡፡
በሕይወትህ
ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1፡5
ለሚያምን
ሁሉ ይቻላል
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakum
Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #እምነት #መስማት #የእግዚአብሄርቃል #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ