ከእርሱ
ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፣6 7
ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው ስለእኛ ነው። ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው እኛ በሃጢያታችን
ምክኒያት ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላላም እንዳንለያይ ነው።
ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ
እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፣21 22
ክርስቶስ ኢየሱስ የሞተው እኛ በሃጢያታችን መሞት የነበረበንን ሞት ነው። ክርስቶስ
የሞተው በእኛ ምትክ ነው። ክርስቶስ የሞተው ለእኛ ነው።
በመጀመሪያ ሰው የተፈጠረው ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላላም እንዲኖር ነበር። በእግዚአብሔር
የተፈጠረው ሃጢያትን የማያውቅ ፍጹም ሰው ነበር።
ሰው ከእግዚአብሔር የተለየው ሃጢያት በሰራ ጊዜ ነበር።
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር
ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። ዘፍጥረት 2፣16 17
ክርስቶስ የመጣው እኛ ወደፊት እንዳንሞት ከእግዚአብሔርም ጋር ለዘላላም እንዳንለያይ
ነው።
ክርስቶስ ሃጢያት ያልተገኘበት ፍጹም ነው። ክርስቶስ መሞት አይገባውም ነበር። ክርስቶስ የሞተው እኛ ሞት ሰለሚገባን ነበር። ክርስቶስ የሞተው እኛን
ከሞት ሊያስነሳን በእኛ ምትክ ነው።
ክርስቶስ የሞተው ለእኛ ትንሳኤን ሊሰጠን ነው።
እኛ ከክርስቶስ ጋር አብረነው ካልተነሳን ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።
የክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ "ከእለታት አንድ ቀን ክርስቶስ ከሞት ተነሳ"
ብለን ብቻ የምናስታውሰው የክርስቶስ ታሪክ አይደለም። የክርስቶስ ትንሳኤ የእኛም ከሙታን የመነሳት ልምምድ ነው። በክርስቶስ ሞትና
ተንሳኤ የምናምን ሁላችን ከሞት ተነስተናል።
ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር
ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት
ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፣5-7
የትንሳኤ በአል የክርስቶስ ብቻ ሳይሆን የእኛም የትንሳኤ በአል ነው።
መልካም የትንሳኤ በአል
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
