I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
Understanding God's special purpose in marriage from God's word is crucial. Achieving the purpose of marriage's first establ...
-
አቢይ የጥሞና ቃል #ስድስት የእግዚአብሔር መንግሥት ሰላም የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡17 እግዚአብሄር ንጉስዋ የሆነ...
-
Man is created in the image of God. Man can only succeed by teaming up with God. A man can’t be neutral. You can’t be successful in Chri...
-
ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና። 1ኛ ዮሐንስ 4፡4 አለም በክፉ ተይዞዋል፡፡ አለም እንዲደግፈንና እንዲያበረታታን አንጠብቅም፡፡ አ...
-
ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ማቴዎስ 5፡10 አለም በክፉ ተይዞአል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ሲያመልክና ሲከተል ከብዙ ሰዎች መካከል ተለይቶ ይወጣል፡፡ በክርስትና ለጌታ ብ...
-
ፍቅር አስደናቂ ነው፡፡ በተለይ ፍቅር ሁሉን ያምናል የሚለውን ቃል ሳሰላስል ነበር ያመሸሁት፡፡ ይህን ቃል ሳሰላስል ጌታ የሰጠኝን መረዳት አብሬያችሁ ልካፈል ወደድኩ፡፡ ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡ 1ኛ ቆሮንጦስ ...
Monday, May 13, 2019
የደስተኝነት ምርጫ
በህይወት ደስተኛ መሆን የእድል ጉዳይ ሳይሆን የምርጫ ጉዳይ ነው:: ሰው ሁሉ ደስተኛ መሆን ይፈልጋል:: ነገር ግን ሰው ሁሉ ደስተኛ የሚያደርገውንነገር አይመርጥም:: እንዳንድ ሰው ደስተኛ ለመሆን ቢፈልግም ደስተኛ የሚያደርጉትን ሳይሆን ደስተኛ የማያደጉትን ነገሮች ስለሚመርጥ ደስተኛ ሳይሆን ጊዜውን ያባክናል::
ክፉ ሀዘን ጉልበትን ያደክማል:: ክፉ ሀዘን የኑሮ መነሳሳትን ይገድለዋል::
እርሱም፡— ሂዱ፥ የሰባውንም ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያም ላልተዘጋጀላቸው እድል ፈንታቸውን ስደዱ፤ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ፡ አላቸው። መጽሐፈ ነህምያ 8:10
ደስተኝነት ለመኖር ለመስራትና ወደህይወት ግባችን ለመድረስ ጉልበት ይሰጠናል::
በህይወት ደስተኛ የማያደርገንን ነገሮች እስካልመረጥን ድረስ ደስተኛ መሆናችን አይቀርም::
ደስተኛ የማያደርጉ ሀሳቦች
1. ራስን ከሌላ ሰው ጋር ማፎካከር
ደስተኛ ላለመሆን አቋራጩ መንገድ በህይወት የተለያየ የህይወት አላማና ስጦታ ያላቸውን ሰዎች ለማወዳደርና ለማበላለጥ መሞከር ነው::
ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። 2ኛ ቆሮንቶስ 10:12
2. ያለፈን ህይወት በፀፀት ለማስተካከል መሞከር
ያለፈ ህይወት አልፎዋል:: ስላለፈ ህይወት መፀፀት ዛሬን መግደል ነው:: ስላለፈ ህይወት መፀፀት ከዛሬ ትላንት ይሻል ነበር ብሎ ዛሬን ማናናቅ ነው::
3. የሌለን ነገር ላይ ማተኮር
የሌለን ነገር ላይ ማተኮር ያለንን ነገር በአግባቡ እንዳንጠቀምበት ያደርገናል:: የሌለን ነገር ላይ ማተኮር ያለንን እንዳናከብረውና እንዳንንቀው ያደርገናል:: የሌለን ነገር እንደማያስፈልገን ምንም ማረጋገጫ የለንም::
4. ያልደረስንበት ደረጃ ላይ ማተኮር
ሁላችንም ህልሞች አሉን:: ነገር ግን አሁን አንዳንዱ ህልማችን እውን ሆኖ እየኖርነው አይደለም ማለት አይደለም:: ከዚህ በፊት ምንም ሆኖልን እንደማያውቅ ምንም አከናውነን እንደማናውቅ የነገ ግባችን ላይ ከመጠን በላይ ማተኮር ደስተኛ ላለመሆን መምረጥ ነው::
5. ከጌታ ውጭ ማተኮር
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄርና ከእግዚአብሄር ጋር እንዲኖር ነው:: ሰው ግን እግዚአብሄርን ካላሰበ ደስተኛ መሆን ያቅተዋል:: ብዙ ደስ የማያሰኙ ነገሮች በዙሪያችን እያሉ በጌታ ደስ መሰኘት ይቻላል::
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ወደ ፊልጵስዩስ 4:4
Subscribe to:
Posts (Atom)