I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገ...
-
Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deessi, maqaa isaas Amaanu'el jettee in mo...
-
ያላችሁም ይብቃችሁ ! አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ። አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤ ወደ ዕብራውያን 13:5 ሰዎች ...
-
ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያ የ መልኩ ይከበራል ፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚ ከ ብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባ...
-
የክህነት ህይወት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ The Life of Priesthood Abiy Wakuma Dinsa
-
We hear this kind of saying from time to time. And we sometimes say it or are tempted to say it, especially after we are betrayed by a ve...
-
Dhalachuun Yesus Raawwii Raajichaa Ture Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deess...
-
እንግዲህ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ። እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። 2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፡1፣3 ኢየሱስ ጌታ ነው ብለን...
Tuesday, February 14, 2023
Saturday, February 11, 2023
አንዳንዶች ከቅንአትና ከክርክር እንኳ ሌሎች ግን ከበጎ ፈቃድ የተነሣ ክርስቶስን ይሰብኩታል፤ እነዚህ ወንጌልን መመከቻ ለማድረግ እንደ ተሾምሁ አውቀው በፍቅር ይሰብካሉ፥ እነዚያ ግን በእስራቴ ላይ መከራን ሊያመጡብኝ መስሎአቸው፥ ለወገናቸው የሚጠቅም ፈልገው በቅን አሳብ ሳይሆኑ ስለ ክርስቶስ ያወራሉ። ምን አለ? ቢሆንም በሁሉ ጎዳና፥ በማመካኘት ቢሆን ወይም በቅንነት ቢሆን፥ ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:15-18
አንዳንዶች ከቅንአትና ከክርክር እንኳ ሌሎች ግን ከበጎ ፈቃድ የተነሣ ክርስቶስን ይሰብኩታል፤ እነዚህ ወንጌልን መመከቻ ለማድረግ እንደ ተሾምሁ አውቀው በፍቅር ይሰብካሉ፥ እነዚያ ግን በእስራቴ ላይ መከራን ሊያመጡብኝ መስሎአቸው፥ ለወገናቸው የሚጠቅም ፈልገው በቅን አሳብ ሳይሆኑ ስለ ክርስቶስ ያወራሉ። ምን አለ? ቢሆንም በሁሉ ጎዳና፥ በማመካኘት ቢሆን ወይም በቅንነት ቢሆን፥ ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:15-18
Thursday, February 9, 2023
Sunday, February 5, 2023
የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን መሪዎች የልብ መነሻ ሃሳብ ይፈተናል!
ሰሞኑን በተከሰተው የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን መሪዎች ግጭት ሰዎች የተለያየ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ እኔም በበኩሌ ያለኝን የግል አስተያየት ለመስጠት ወደድኩ፡፡
የእኔ አስተያየት ግን ወገንተኝነት ያለበት እንዳይሆን
፣ ከዚህም ከዚያም ወገን ያልወገነ እንዲሆን ይልቁንም ከእግዚአብሄር ወገን የሆነ እንዲሆን የእግዚአብሄር ፍላጎት ምንድነው? የሚለውን
ከእግዚአብሄር ቃል ተመለከትኩ፡፡
እግዚአብሄር በሰዎች ጦርነት ውስጥ በስሜት ተነሳስቶ
ዘሎ የሚገባ ሞኝ አምላክ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የራሱ ቋሚ መመሪያ ያለው የመመሪያ አምላክ ነው፡፡
እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን? አለው። እርሱም፦ አይደለሁም፤ እኔ የእግዚአብሔር
ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ አለ። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 5፡13-14
እግዚአብሄር የማንም ወገንተኛ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር
እንደሰው የሚያየው ድርጊትን ብቻ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሰውን የልብ መነሻ ሃሳብ /ሞቲቭ/ ይመለከታል፡፡
በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። የያዕቆብ መልእክት 4፡1-3
ሰው ፊትን ያያል እግዚአብሄር ግን ልብን ይመዝናል፡፡
ሰው ጎሽ ያለውን ድርጊት እግዚአብሄር የልቡን መነሻ ሃሳብ አይቶ ድርጊቱን ይንቀዋል፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ልብ ይመዝናል፡፡
ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16፡7
እግዚአብሄር የእነዚህም የእነዚያም የድርጊታቸውን
መነሻ ሃሳብ መዝኖ ወይ ይንቀዋል ወይ ያከብረዋል፡፡
ምንም መልካም የሚመስል ድርጊት ቢደረግ የተደረገው
ከራስ ወዳድነት የልብ መነሻ ሃሳብ ተነስቶ ከሆነ እግዚአብሄር ያዝንበታል እንጂ አይደሰትበትም፡፡ ምንም መልካም የሚመስል ድርጊት
ቢደረግ የተደረገው ከትእቢት እና ከማን አለብኝነት የልብ መነሻ ሃሳብ ከሆነ እግዚአብሄርን ያስቆጣዋል፡፡ ምንም መልካም የሚመስል
ድርጊት ቢደረግ የተደረገው ለራስ ስም ዝና እና ጥቅም ከሆነ እግዚአብሄር አይወደውም፡፡
የተደረገው ነገር የተደረገው ለፍቅር ፣ ለአንድነት
እና በመተሳሰብ ከሆነ ግን እግዚአብሄርን ደስ ያሰኘዋል፡፡
በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ
ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡1-3
የተደረገው ነገር የተደረገው ለእግዚአብሄር ህዝብ
በቅንነት ከመጨነቅ ከሆነ እግዚአብሄር ይደግፈዋል፡፡
እንደ እርሱ ያለ፥ ስለ ኑሮአችሁ በቅንነት የሚጨነቅ፥ ማንም የለኝምና፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡20
የተደረገው ድርጊት ለመንጋው እረኛ ለመሆን ግልገሎቼን
አሰማራ ፣ ጠቦቶቼን ጠብቅ እና ለበጎቼን አሰማራ የሚለውን የኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዝ ለመጠበቅ ከሆነ እግዚአብሄርን ደስ ያሰኘዋል፡፡
ምሳ ከበሉ በኋላም ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ግልገሎቼን አሰማራ አለው። ደግሞ ሁለተኛ፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው። ሦስተኛ ጊዜ፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። ሦስተኛ፦ ትወደኛለህን? ስላለው ጴጥሮስ አዘነና፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ኢየሱስም፦ በጎቼን አሰማራ። የዮሐንስ ወንጌል 21፡15-17
የተደረገው ነገር የተደረገው ህዝቡ በሚረዳው ቋንቋ
የእግዚአብሄርን ቃል እንዲሰማ እንዲረዳ እና ራሱን ለእግዚአብሄር እንዲሰጥ ከሆነ መልካም የተቀደሰ የልብ መነሻ ሃሳብ ነው፡፡
የተደረገው ነገር የተደረገው ግን ለጥቅም ለዝና
ለክብር ከሆነ በማንም ወገን ይደረግ እግዚአብሄር ይህንን ንፁህ ያልሆነ የልብን መነሻ ሃሳብ ይፀየፈዋል፡፡
የተደረገው ነገር የተደረገው በሰማያዊ ሃሳብ ሳይሆን
በምድራዊ ሃሳብ ከሆነ መፅሃፍ ቅዱስ ዋጋቸውን በምድር ተቀብለዋል እንደሚላቸው ምስኪን ሰዎች ከሆነ እግዚአብሄር ከድርጊቱ ጋር አይተባበር፡፡
በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡2
ሰው የእግዚአብሄር ወገን መሆን ከፈለገ የልቡን
መነሻ ሃሳብ መፈተሽ መመርመር ይኖርበታል፡፡ ሰው የእግዚአብሄር ወገን መሆን ከፈለገ ልቡን አጥርቶ በእግዚአብሄር መንገድ እርሱን
ለማገልገል መጨከን ይገባዋል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa