I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያ የ መልኩ ይከበራል ፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚ ከ ብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁ...
-
Dhalachuun Yesus Raawwii Raajichaa Ture Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deess...
-
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገ...
-
https://youtu.be/VhF0pSsp14I በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን
Tuesday, January 31, 2023
Wednesday, January 25, 2023
Thursday, January 19, 2023
Wednesday, January 18, 2023
Tuesday, January 17, 2023
አሕዛብ ለምን ያጕረመርማሉ? ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ? የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል። በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል። መዝሙር 2:1-5
አሕዛብ ለምን ያጕረመርማሉ? ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ? የምድር ነገሥታት ተነሡ፥አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል። በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜበቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል። መዝሙር 2:1-5
Sunday, January 15, 2023
Saturday, January 14, 2023
የሁለቱ ቅርጫቶች ወግ
አንድ ልቤን የነካኝን ታሪክ ልንገራችሁ፡፡
እግዚአብሄር ለአንድ አገልጋይ ስለአንዲት የምትፀልይ ሴት ራእይ አሳየው፡፡ በራእዩ ውስጥ ሁለት ቅርጫቶችን ያያል፡፡ አንዱ ቅርጫት ሙሉ ነው አንዱ ቅርጫት ግን ውስጡ ያለበት ነገር እጅግ በጣም ትንሽ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ይህ ምንድነው ? ብሎ ስለትርጉሙ ሲጠይቅ ስለሁለቱ ቅርጫቶች እንዲህ ሲል ተናገረው፡፡ እነዚህ ቅርጫቶች የዚህች ሴት የፀሎት እና የምስጋና ህይወትዋ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ይህች ሴት መፀለይ ታውቃለች፡፡ ካለማቋረጥ አብዝታ ትፀልያለች ትጮኻለች፡፡ ይህ የምትመለከተው ሙሉው ጭርጫት የፀሎት ህይወቷ ነው፡፡ ይህ የምትመለከተው እጅግ በጣም ትንሽ ነገር ያለበት ቅርጫት ደግሞ የምስጋና ህይወቷ ነው፡፡ ይህች ሴት መፀለይ ታውቃለች እንጂ ማመስገን አታውቅም፡፡ ስለዚህ ፀሎትዋ እንደሚገባው ውጤታማ አይደለም፡፡
ይህች ሴት ማመስገን ስትጀምር እና የምስጋና ቅርጫትዋ እየሞላ ሲደሄድ የፀለየችው ፀሎትዋ እየተመለሰ ይሄዳል ብሎ እግዚአብሄር አስረዳው፡፡
ይግህ ታሪክ ስለ እያንዳንዳችን የፀሎት ህይወት ወሳኝ ነገርን ያስተምረናል፡፡
ሰው መፀለዩን እንጂ እንዴት በምስጋና ልብ መፀለይ እንዳለበት ካላወቀ በፀሎት ህይወቱ ውጤታማ ሊሆን አይችልም፡፡ ከፀለየ በኋላ እንዴት በማመስገን መቀጠል እንዳለበት የማይረዳ ሰው ፀሎቱ ፍሬያማ መሆን አይችልም፡፡
ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ማንኛውም ግንኙነት በምስጋና ልብ መሆን አለበት፡፡ በአጠቃላይ ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ግንኙነት በትህትና ለእግዚአብሄር አምላክነት እና መልካምነት እውቅና በመስጠት ካልሆነ ውጤታማ አይሆንም፡፡
በፀሎትም ወደ እግዚአብሄር መቅረብ የህይወታችን እረኛ እንደሆነ ፣ የሚያሳጣን እንደሌለ ፣ በእርሱ አቅርቦት በየእለቱ እንደምንኖር እውቅና መስጠት ይጠይቃል፡፡ ወደ እግዚአብሄር ስንቀርብ በማጉረምረም መሆን የለበትም፡፡ ወይም ደግሞ እግዚአብሄር በትክከል እንዳልያዘን ፣ ምንምም ነገር አድርጎን እንደማያውቅ መቅረብ የለብንም፡፡ ወደ እግዚአብሄር ስንቀርብ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ነገር ሊያደርግልን እንደሆነ በማንጎራጎር ከሆነ ለአምላክነቱ የሚገባውን እውቅና ስላልሰጠ በፀሎታችን እግዚአብሄር ደስ አይሰኝም፡፡
በደስታም ለእግዚአብሔር ተገዙ፥ በሐሤትም ወደ ፊቱ ግቡ። እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ፤ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን። ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፤መዝሙረ ዳዊት 100፡2-4
ወደ እግዚአብሄር ስንቀርብ እግዚአብሄር በመልካምነቱ እያጠገበን እንደሆነ እውቅና በመስጠት ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ አሁንም በጸሎት ወደፊቱ የቀረብነው አንድ ተጨማሪ ነገር እንዲያደርግልን ስለፈለግን እንጂ ከዚህ በፊት እድርጎልን እንደማያውቅ በማጉረምረም መሆን የለበትም፡፡ አንተ ግን ለእኔ የማታደርገው ለምንድነው? በሚል በማጉረምረም በትእቢት ልብ ወደፊቱ ለመቅረብ ከሞከርን ከእግዚአብሄር መልስን የሚያመጣ ጸሎት መፀለይ እንችልም፡፡
ከፀለይን በኋላም እግዚአብሄርን በማመስገን መቀጠል አለብን፡፡ በእምነት የፀለይነው ፀሎት እንደተቀበልን ካመንን ከማመስገን ውጭ ሌላ ምንም ነገር ሊመጣልን አይችለም፡፡ ከፀለይን በኋላ ሁኔታው ሙሉ በሙሉ በተፈጥሮአዊ አለም ተፈጽሞ በህይወታችን እስክናይ ድረስ በማመስገን መቀጠል አለብን፡፡
ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። የማርቆስ ወንጌል 11፡24
ከመፀለያችን በፊትም ከፀለይን በኋላም ያለን የምስጋና ልብ ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን ጤናማ ግንኙነት ያሳያል፡፡ ከመፀለያችን በፊትም ከፀለይን በኋላም ያለን የምስጋና ልብ በእግዚአብሄር ፊት የጸለይነው ፀሎት እንዲመለስ ያደርጋል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
Wednesday, January 11, 2023
Friday, January 6, 2023
Subscribe to:
Posts (Atom)