ልናጣው የማንችለው ነገር ሁሉ የእኛ አይደለም
በህይወታችን ዘመን ብዙ በረከቶች ወደ ህይወታችን ይመጣሉ:: እኛን ለመባረክና እና ለመጥቀም እግዚአብሔር ልዩ ልዩ መንገዶችን ይጠቀማል:: በህይወታችን ያለውን አላማውን ለመፈጸም እግዚአብሄር በብዙ አይነት እና በብዙ መንገድ የሚጠቀምባቸው ነገሮች ሁሉ የጊዜው ናቸው እንጂ ለዘላለም አይደሉም::
ከእግዚአብሔር ውጭ ምንም ቋሚ ነገር የለም:: ከእግዚአብሔር ውጭ የሚታየው ነገር ሁሉ ሃላፊ ነው::
ቋሚ ያልሆነን ነገር እንደ ጊዜያዊነቱ በትክክል መያዝ ከብዙ ጭንቀት ያድናል::
ከእግዚአብሔር ውጭ ይህን ካላገኘሁ አልኖርም የምንለው ምንም ነገር መኖር የለበትም::
እግዚአብሔር የሚሰጠንን ነገሮች ጨምሮ አንድ ቀን እንደማንለያቸው አድርገን ውስጣችን ማስገባት ችግርን መጋበዝ ነው:: የራሳችንን ማንነትና ነፃነት እስከምናጣ ድረስ ሁኔታዎችን ውስጣችን መክተት ጊዜያዊዉን ነገር ስንለየው ስቃይ ውስጥ መግባት ያስገባናል:: የነገሮችን ጊዜያዊነትና ልካቸውን ማወቅ ብልህነት ነው፡፡ ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ የሚለውን ቃል መከትል ጥበብ ነው::
አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም። 2ኛ ጢሞቴዎስ 4:5
ለዘላለም ከሚኖረው ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ ሁኔታዎችን ወደ ውስጣችን አለማስገባትና በውጭ መጠበቅ ስንለይ ከሚመጣ የመለያየት ስቃይ ይጠብቀናል::
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ . . . የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4:17-18
ብዙ ጊዜ ሰይጣን የሚያስፈራራንና እስራት ውስጥ የሚከተን ይህን ነገር ብታጣውስ ብሎ በማስፈራራት ነው:: እግዚአብሔርን አልጣው እንጂ ካለእርሱ መኖር የማልችለው ምንም ነገር የለም ካልን ለሰይጣን እድል ፈንታ አንሰጠውም:: ከእግዚአብሔር ውጭ ካለእርሱ መኖር አልችልም የምንለው ነገር ካለ በዘመናችን ሁሉ በፍርሃት ባርነት ውስጥ እንቆያለን ::
ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡27
በምንም ነገር በእውነት ተጠቃሚ የምንሆነው ላጣው አልችልም ብለን የምናስበውን ነገር ከሌለና ማንኛውንም ነገር ለማጣት ከተዘጋጀን ብቻ ነው::
ይህን ካጣኽው መኖር አትችልም የሚለው በፅኑ ልንቃወመው የሚገባ የሰይጣን ድምፅ ነው::
ልንይዘውና ልንጠቀምብት እንጂ ምንም ነገር ሊይዘን እና ሊቆጣጠረን አይገባም::
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡29-31
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #በመጠኑ #እንደፈቃዱ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ኢየሱስ ለእኛ ሰው ሆኖ ወደምርድ ስለመጣ ፍፁም ምሳሌያችን ነው፡፡ ማንንም ባንከተል ኢየሱስን መከተል አለብን፡፡ ማንም ምንም የሚጎድለው ባህሪ ቢኖር ኢየሱስ በባህሪው ፍፁም ነው፡፡ ኢየሱስ ሙሉ ለሙሉ ልንከተለው የምንች...
-
በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡8 የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵ...
-
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7 ፡ 29 የትዳር አላማ አንዱ ...
-
ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል። ዓመፀኝነት እንደ ...
-
እግዚአብሄር የአላማ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን ለክብሩ ነው፡፡ የፈጠረን እግዚአብሄር በህይወታችን ምን እንደምንሰራ ግድ ይለዋል፡ ፡ እግዚአብሄር ምን እንደምንሰራ ግድ እንደሚለው ሁሉ ለምን ምክኒያት እንደም...
-
ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን ? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ...
-
የሰይጣን አላማው መስረቅ ማረድና ማጥፋት ነው፡፡ ሰይጣን ከመስረቅ ከማረድና ከማጥፋት ውጭ ሌላ ምንም አላማ የለውም፡፡ ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ የዮሐንስ ወንጌል 10፡1...
-
እኛ በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት አምነን የዳንን ሁላችን እግዚአብሄር በምድር ላይ ለሰጠን የቤት ስራ በእግዚአብሄር መንፈስ ተቀብተናል፡፡ ካለ እግዚአብሄር መንፈስ እርዳታ የእግዚአብሄርን ስራ መስራት አይቻልም፡፡ የእ...
No comments:
Post a Comment