Saturday, September 28, 2024

ሶስቱ የማይመለሱ ፀሎቶች

 

ሶስቱ የማይመለሱ ፀሎቶች

  1. በስጋ የሚፀለዪ ፀሎቶች 

ፀሎት ክእግዚአብሄር ከአባታችን የምንቀበልበት መንገድ  ቢሆንም የሚያስፈልገንን እንጂ የራስወዳድነታችንን እና የስግብግብነታችንን ፍላጎት የምናስፈፅምበት መድረክ አይደለም:: መሰረታዊፍላጎታችንን እንጂ ቅንጦታችንን የምናሟላበት መሳሪያ አይደለም::              

በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉበብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? 2 ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱምትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተአይሆንም፤ 3 ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም።የያዕቆብ መልእክት 4:1-3

2. በስንፍና የሚፀለዪ ፀሎቶች 

ፀሎት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከቃሉ ፈልገን እንደ እግዚአብሔር ቃል በመፀለይ የምንቀበለው እንጂበስንፍና እጃችን ላይ የሚወድቅ እድል አይደለም::            

14 በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። 1 የዮሐንስመልእክት 5:14

3. በጥላቻ ይቅር ባለማለት የሚፀለዪ ፀሎቶች

ፀሎት የእኛን ጥላቻ ማስፈፀሚያ መሳሪያ አይደለም:: ፀሎት በፍቅር የመባረኪያ እንጂእግዚአብሔርን የእኛ ወገን አድርገን የማንቀበለውን ሰው መርገሚያ መሳሪያ አይደለም::

25 ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።

26 እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።የማርቆስ ወንጌል 11:25-26


አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


#ፀሎት #ፈቃዱ #መልስ #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ሚስት #መዳን#መፅሃፍቅዱስ #ባል #እምነት #ወንድ #ፍቅር #ትዳር #ሰላም #ሴት #አቢይ #አቢይዋቁማ#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ


No comments:

Post a Comment