መዝሙረ
ዳዊት 136
|
||
እግዚአብሔርን
አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
|
||
የአማልክትን
አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
|
||
የጌቶችን
ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
እርሱ
ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ሰማያትን
በብልሃት የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ምድርን
በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ብቻውን
ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ለፀሐይ
ቀንን ያስገዛው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ለጨረቃና
ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ከበኵራቸው
ጋር ግብጽን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
እስራኤልንም
ከመካከላቸው ያወጣ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
በጸናች
እጅ በተዘረጋችም ክንድ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
የኤርትራን
ባሕር በየክፍሉ የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
እስራኤልን
በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ፈርዖንንና
ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ሕዝቡን
በምድረ በዳ የመራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ታላላቅ
ነገሥታትን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ብርቱዎችንም
ነገሥታት የገደለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
የአሞራውያንን
ንጉሥ ሴዎንን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
የባሳንን
ንጉሥ ዐግን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ምድራቸውን
ርስት አድርጎ የሰጠ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ለባሪያው
ለእስራኤል ርስት፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
|
||
እኛን
በመዋረዳችን አስቦናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
|
||
ከጠላቶቻችንም
እጅ አድኖናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና
|
||
ለሥጋ
ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
|
||
የሰማይን
አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
|
I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
No comments:
Post a Comment