apostle Abiy Wakuma Dinsa
I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Thursday, August 17, 2017
የአጋርነት ፈተና
አጋርነት እጅግ ታላቅ ጥቅም አለው፡፡ በአጋርነት ውስጥ የተቀመጠው በረከት ጥልቅ ነው፡፡ በአጋርነት ውስጥ እጅግ ታላቅ በረከት እንደመቀመጡ ሁሉ ፈተናዎችም ደግሞ አሉት፡፡ መልካም ነገር ርካሽ እንዳልሆነና በቀላሉ እንደማይገኝ እንዲሁ አጋርነት ትጋትንና ትህትናን ይጠይቃል፡፡
የአጋርነት ፈተናዎች የሚመጡት አጋሩ በሚደክምበት ጊዜ ነው፡፡ የአጋርነት ትክክኛውም ፈተና ያለው በጥንካሬ ሳይሆን በድካም ወቅት ነው፡፡ የአጋርነትም ጥንካሬው በእውነት የሚፈተነው በአስቸጋሪ ጊዜ ነው፡፡
በመከራ
ቀን
ብትላላ
ጉልበትህ
ጥቂት
ነው። ምሳሌ 24፡10
ምክኒያቱም አጋርነት የታቀደው የሌላን ብርታት ለመድገም ሳይሆን የሌላውን ድካም ለመሸፈን ነው፡፡ የአጋርነት አላማ ሌላው በሚደክመበት ለመሙላት ነው፡፡
የከነዓን
አባት
ካምም
የአባቱን
ዕራቁትነት
አየ፥
ወደ
ውጭም
ወጥቶ
ለሁለቱ
ወንድሞቹ
ነገራቸው።
ሴምና
ያፌትም
ሸማ
ወስደው
በጫንቃቸው
ላይ
አደረጉ፥
የኋሊትም
ሄደው
የአባታቸውን
ዕራቁትነት
አለበሱ፤
ፊታቸውም
ወደ
ኋላ
ነበረ፥
የአባታቸውንም
ዕራቁትነት
አላዩም።
ዘፍጥረት
9
፡
22-23
ካም የአባቱን ራቁትነት አየ፡፡ የአባቱ ራቁትነት የራሱ ራቁትነት እንደሆነ አልተገነዘበም፡፡ የአባቱን ድክመት መሸፈን የራሱን ድክመት መሸፈን መሆኑን አልተገነዘበም፡፡ ማንም መንገደኛ የሰውን ራቁትነት መግለጥ ይችላል፡፡ የሌላውም ራቁትነት መግለጥ በጣም ቀላል ነው፡፡ የሌላውን ራቁትነት መሸፈን ግን ትጋትና ትህትናን የሚጠይቅ ጨዋነት ነው፡፡
ሴምና ያፌት የአባታቸው ራቁትነት የራሳቸው ራቁትነት መሆኑን ስለተረዱ ለመሸፈን ፈጠኑ፡፡
የአጋርን ድካም ማየት ቀላል ነው፡፡ የአጋርን ድካም መግለጥ ያን ያህል አይከብድም፡፡ ማንም መንገደኛ የአጋርን ድካም መግለጥ ይችላል፡፡ የአጋር ድካም የእኔ ድካም ነው ማለት ግን ከፍ ያለ መረዳት ነው፡፡ የአጋሬን ድካማ ያየሁት እንድሸፍነው እንጂ እንድገልጠው አይደለም ማለት ጨዋነት ነው፡፡ የአጋሬን ድካም እኔ ካልሸፈንኩ ማን ይሸፍነዋል? ማለት ቤተሰባዊነት ስሜት ነው፡፡
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#
ኢየሱስ
#
ጌታ
#
ህብረት
#
አጋርነት
#
አብሮማደግ
#
የጋራ
#
ሚስት
#
ባል
#
ቤተሰብ
#
ወንድ
#
ሴት
#
ዘር
#
መሰረታዊፍላጎት
#
ቤተክርስትያን
#
አማርኛ
#
ስብከት
#
መዳን
#
መፅሃፍቅዱስ
#
ሰላም
#
አቢይ
#
አቢይዋቁማ
#
አቢይዋቁማዲንሳ
#
እወጃ
#
መናገር
#
ፅናት
#
ትግስት
#
መሪ
No comments:
Post a Comment
‹
›
Home
View web version
No comments:
Post a Comment